በረዥሙ የሀገራችን ታሪክ ውስጥ ኢትዮጵያ ፈተና ውስጥ የገባችባቸው ጊዜያት ብዙ ናቸው። ርሃብ፣ ድርቅ፣ ወረርሽኝ፣ የውጭ ወራሪ፣ የእርስ በእርስ ጦርነት፣ ወዘተ ተከስተው ሁሉንም አልፈናል። በፈተናዎቻችን ሁሉ እንደ ሕዝብ መገለጫችን ሆኖ የዘለቀ የዛለ ጉልበት፣ የተፈታ ትጥቅ፣ የላላ አንድነት የለንም። ይልቁንም በውጣ ውረዶች ውስጥ ተፈትኖ ያለፈ ሕዝባዊ አንድነት እየፈጠርን የጋራ ችግሮቻችንን በትብብር አሸንፈን ወጥተናል።
ሀገራዊ የትብብር፣ የአንድነት እና የጋራ ጥረቶቻችንን ለማዳከም የሚፈታተኑን ችግሮች በየዘመናቱ አጋጥመውናል። ብዙ የአርበኝነት ትጋት እና መስዋእትነት የነበረንን ያህል የባንዳዎች ክህደትም በየዘመናቱ ተገዳድረውናል። ወደ ፊት በስኬት ለመሮጥ በምናደርገው ጥረት ወደ ኋላ የሚጎትቱን ጠፍተው አያውቁም። አንድ ለመሆን የምንውተረተረውን ያህል ሊከፋፍሉን የሚፈልጉ ተኝተው ያደሩበት ጊዜ የለም ።
በየዘመናቱ ስለሀገር እና ሕዝብ የሚያስቡ የትኛውንም ዓይነት ዋጋ ለመክፈል ወደኋላ የማይሉ በርካቶች እንደነበሩ ሁሉ ስለግል ጥቅማቸው ሀገርና ሕዝብን ብዙ ዋጋ ያስከፈሉ ነበሩ። የሚያስገርመው ግን ሁሌም ችግር ፈጣሪዎቻችን ከችግሮቻችን በታች ሆነው ክፉ ቀንን ስናልፍ ዛሬ ላይ መድረሳችን ነው ።
ዛሬም ሀገራችን ወቅቱ በፈጠረው ችግር ውስጥ ነች፣ ዓለምን የፈተነው የኮሮና ወረርሽኝ ከፖለቲካችን አለመዘመን ጋር ተደምሮ እየፈተናት ነው። ፈተናው መላውን የሰው ልጅ ዋጋ እያስከፈለ ቢሆንም፣ ለኛ ግን ፟ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንዲሉ ከስድስተኛው ሀገራዊ ምርጫ ጋር በተያያዘ ፖለቲከኞቻችን እየፈጠሩት ካለው ሁከት ጋር ተዳምሮ ለሀገራችን እና ለሕዝባችን ድርብ ፈተና ሆኗል።
ኮሮና እስካሁን ባለው እውነታ ከጤና አደጋነቱ ባለፈ በሀገራት ኢኮኖሚ፣ፖለቲካና ማህበራዊ እንቅስቃሴዎች ላይ መጠነ ሰፊ ጫና እያሳደረ ነው። ጫናው እኛን ከኛ በብዙ ርቀት ባሉ የበለጸጉት ሀገራትንም አስጨንቋል፤ መታመኛቸውን በሙሉ ዋጋ ቢስ አድርጎባቸውል። እልፍ ሕይወት ቀጥፏል፣ ለቁጥጥር አስቸግሮና የቤት ውስጥ ተቀማጭ ምርኮኛ አድርጓቸዋል፣ ለቁጥጥር ከብርቱ ተቋሞቻቸው በላይ ሆኖ መላ ከፈጣሪ እስኪለምኑ አድርሷቸዋል።
ችግሩ እንኳን ፖለቲከኞቻችን እየፈጠሩት ያለው የምርጫ ሁከት ተደምሮበት፤ ብቻውን በእኛ ሀገር ተጨባጭ ሁኔታ ሊፈጥር የሚችለው ምስቅልቅል ምን ሊመስል እንደሚችል መገመት ለማንም ጤነኛ አእምሮ ላለው ሰው ብዙ የሚከብድ አይደለም
ምርጫ ሕገመንግሥታዊ በሆነ መልኩ ወደ ሥልጣን መምጫ መንገድ ነው። ሥልጣን ደግሞ ሀገርና ሕዝብን በተቀመጠ የሕግ አግባብ የማስተዳደሪያ መሣሪያ ነው። ሀገርና ሕዝብን ታሳቢ ያደረገ ነው። ከዚህ ያለፈ አይደለም። ይህ ሊሆን የሚችለው ከሁሉም በላይ ሕዝብ ሲኖር ነው ። ምርጫ ማካሄድ የሚያስችል የተረጋጋ ሥነ ልቦና ሲኖረው ጭምር። ሕዝብ እና ሀገር ከፍተኛ በሆነ ስጋት ውስጥ ባሉበት ሁኔታ ምርጫን አጀንዳ አድርጎ ሜዳ መሙላት ኃላፊት ከሚሰማው ዜጋ ሆነ የፖለቲካ ድርጅት የሚጠበቅ አይደለም።
ከዚህም ባለፈ የችግር ግምገማ እና ትንተናውን ከፖለቲካ ጨዋታ ጋር በማዳቀል፣ ምርጫውን አሁን ካልተካሄደ ፣ በራሴ ክልል አካሂዳለሁ ማለትም ኢ ሕገ መንግሥታዊ ከመሆኑም በላይ፤ ከሰብአዊ የሞራል እሴት አንጻር ትንሽ በጣም ትንሽ የሚያደርግ ነው።
ከመስከረም 30 በኋላ የመንግሥቱ አካል ካልሆንን የመንግሥቱ ቅቡልነት ጥያቄ ውስጥ ይሆናል፤ ያኔ «አዛዥ ታዛዥ የለም» በሚል የኮሮና በሽታ ከፈጠረው ስጋት በላይ ሀገራዊ ስጋት በመሆን ወደ ሥልጣን ለመምጣት የሚተጉ ኃይሎች፤ ስለ ሀገርና ሕዝብ አፍ ሞልቶ ለማውራት የቱን ያህል ሞራል እንደሚኖራቸው ለማሰብ የሚከብድ ነው። በግርግር ወደ ፖለቲካ ሥልጣን ለመምጣት የሚደረግ ጥረት ከሁሉም በላይ ከግርግር አተርፋለሁ የሚለውን የከፋ ዋጋ እንደሚያስከፍለው በአግባቡ አሁን ላይ ሆኖ ማሰብ የሚጠቅም ነው።
ለፖለቲካ ትግል፣ ሂሳብ ለማወራረድ፣ እና አብላጫ ተቀባይነት ለማግኘት በሚመስል መልኩ የሚታየው የፖለቲካ ግርግር የሕዝቡን ፍላጎትና የሀገርን ቀጣይ ህልውና ታሳቢ ያደረገ፤ የፖለቲካ ሥልጣን ከመሻት በላይ ቦታ ሊሰጠው የተገባ ነው ። እንዲህ ያለው ኃላፊነት የጎደለው፣ ሀገራዊ ትብብርና መደጋገፍን የሚያሳንስ የፖለቲካ ትግል ሀገርን ከፖለቲካ ፍላጎቶች በታች የማድረግ የትንሽነት መገለጫ ነው።
ሀገር ማለት ሕዝብ፣ ዳር ድንበር፣ ሉዓላዊነት፣ መንግሥት እና የተቋማት ቅቡልነት ነው። አሁን እንደገጠመን ዓይነት ሀገራዊ ችግር ሲከሰት እነዚህ የሀገር መገለጫ ወሳኝ ጉዳዮችን ታሳቢ ያደረገ አማራጭ መከተል አስፈላጊ ነው። ፖለቲከኞቻችን ሀገራዊ ችግርን ከሕዝቡ ጥቅምና ፍላጎት፣ ከሀገር ሉዓላዊነት እና ከሕገመንግሥታዊ ሥርዓት አንጻር ለመፍታት ትልቁን ኃላፊነት ሊወስዱ ይገባል።
የሕዝቡን ፍላጎት እና የሀገርን ዘላቂ ጥቅም ግምት ውስጥ ከማስገባት ይልቅ ርካሽ የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት የሚደረጉ ሩጫዎች እንወክለዋለን የምትሉትን በየትኛውም ስፍራ ያለ ኢትዮጵያዊን የሚመጥን አይደለም። ሀገርና ሕዝብን ትንሽ የሚያደርግ ዘመን አመጣሽ ነቀርሳ ነው። ሀገርን/ሕዝብን ከፖለቲካ ፍላጎቶች በታች የሚያደርግ መጪውን ትውልድ አንገት የሚያስደፋ፤ ሊታረም የሚገባው አሁናዊ የፖለቲካ ስብራታችን ነው።
ወቅቱ ፖለቲከኞቻችን ከፖለቲካዊ ገበያ ወጥተው የሕዝባችንን ፍላጎት፣ ስጋትና ተስፋውን ተረድተው ፤ እራሳቸውን ለዚህ ታሪካዊ ወቅት በሚመጥን መልኩ አደርጅተው በከፍተኛ ኃላፊነት መንቀሳቀስ ይጠበቅባቸዋል። ፖለቲካውን ከሀገር በታች አድርገው ሊሰሩም ይገባል!!!።
አዲስ ዘመን ግንቦት 3/2012
ፖለቲካውን ከሀገር በታች አድርጉት!!