በታኅሣሥ ወር 2019 ዓ.ም ሁዋን በተሰኘችው የብዙ ሚሊዮን ህዝብ መኖሪያዋ የቻይና ከተማ የተከሰተውና በጉሮሮ አልፎ ሳምባን የሚጎዳና ወደ ሞትም ሊያደርስ የሚችለው ኮሮና ወይም ኮቪድ 19 በመባል የሚታወቀው አደገኛ ቫይረስ የዓለምን ህዝብ የመንፈስ ጭንቀት ውስጥ ከትቶና ከጤንነት መቃወስ አልፎ ከፍተኛ የሆነ አሉታዊ ኢኮኖሚያዊና ባህላዊ ተፅዕኖ እያሳደረ ነው።
ኮረና በመባል የሚታወቀው ይህ ቫይረስ በ2003 ዓ.ም እንደዚሁ በቻይና ምድር ከተከሰተው ሳርስ ከሚባለው ቫይረስ ጋር ዝምድና ቢኖረውም፣ ኮቪድ 19 በመባል የሚታወቀው ይህ አዲስ ቫይረስ ቀደም ብለው ከተከሰቱት እንደ ሳርስ ከመሳሰሉት የኮረና ዘመዶች ጋር ሲነፃፀር በዓይነቱ የተለየና በጣምም አደገኛ እንደሆነ ሊደረስበት ተችሏል። ይህንን በመረዳት የዓለም የጤና ድርጅት በሁዋን ከተማ ከሚገኘው ቅርንጫፉ መረጃዉ ከደረሰውና ብዙ ሰዎችንም እያጠቃ ከመምጣቱ ጋር በተያያዘ በጥር ወር 2020 ዓ.ም ዓለም አቀፋዊ ተፅዕኖ ሊኖረው የሚችል አደገኛ ቫይረስ ነው የሚል ድምዳሜ ላይ ደርሷል። ይኸው የጤና ጥበቃ ድርጅት በጥር ወር 30/2020 ዓ.ም ዓለምን ሊያዳርስ የሚችል የወረርሽኝ(Pandemic) በሽታ ነው በማለት ለመንግሥታት አስታውቋል።
ስለቫይረሱ ምንጭና መራባት የተለያዩ ትንታኔዎች (Theories) ይሰጣሉ። አብዛኛዎች ተመራማሪዎች የኮቪድ 19 መነሻ የሌሊት ወፍ ናት ብለው ሲናገሩ፣ አንዳንዶች ደግሞ በእግሮቿ የምትንቀሳቀስ፣ ሰውነቷ እንደቀበቶ የተተለተለ (Armadillo) የተባለች ለየት ያለች እንስሳ የቫይረሱ ምንጭ መሆኗን ይናገራሉ። ምንም ተባለ ምን የኮሮና ቫይረስ የዓለማችን ትልቁ ዜናና የሰው ልጆች ስጋት ሆኖ ቀጥሏል። እንደ ጆን ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ መረጃ በአሁኑ ወቅት የኮሮና ቫይረስ ከ167 በላይ የዓለም አገራትን አዳርሶ፣ 3 ሚሊዮን 682 ሺህ 968 ሰዎችን አጥቅቷል። ለ257 ሺህ 906 ሰዎች ህልፈትም ምክንያት ሆኗል።
ይህ እውነታ የሚያሳየን አሁንም ድረስ የኮሮና ወረርሺኝ ቅርባችን ሆኖና አድፍጦ የሚሊዮኖችን ህይወት ሊነጥቅ እያደባ መሆኑን ነው። እውነታው ይህ ሆነ እያለ ግን እንደ አገርና እንደ ህዝብ ያለንበት ሰሞናዊ ሁኔታ እጅግ አሳሳቢና ለችግር የማጋለጥ ዕድሉ ከፍተኛ ሆኖ ይታያል። በተለይም ባለፈው ሳምንት የወጡ ሪፖርቶችን በተሳሳተ መንገድ
በመረዳት መዘናጋቱ ማየሉን አካባቢያችንን በቀላሉ በመቃኘት የምንረዳው እውነታ ነው።
የኮሮና ወረርሺኝ በአገራችን መከሰቱ በተሰማ ጊዜ በየቦታው ሲደረጉ የነበሩ የጥንቃቄ ዕርምጃዎች ዛሬ ዛሬ ላይ እየላሉ አንዳንዶቹም ጭራሽ እየተረሱ ነው። ለማሳያም ያህል በበጎ ፈቃደኞች በየቦታው ሲደረጉ የነበሩ የእጅ መታጠቢያዎችን የማስቀመጥና ሰዎች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ የማስተማሩ ሁኔታ በመዳከም ላይ መሆኑ እየታየ ነው። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ እንዳስታወቀውም በተለይም በህዝብ ማመላለሻ ሚኒባሶች የአፍ መሸፈኛ ማስክ ሳያድርጉ የሚጠቀሙ ተጓዦች ቁጥር ከፍተኛ ነው።
በካፍቴሪያዎች፣ በፍራፍሬ ጭማቂ ቤቶችና ምግብ ቤቶችም እጅብ ብሎ መታየቱና በአንድ ጠረጴዛ ላይ ከሦስት ሰው በላይ ሆኖ መቀመጥ ይስተዋላል። በገበያ ቦታዎችና መናኸሪያዎች አካባቢ የሚታየው የህዝብ ትፍግፍግም አጅግ አስደንጋጭ ነው። ትምህርት ተዘግቶ ተማሪዎች በቤታቸው እንዲሆኑ የተደረገውም ከዚሁ አስከፊ ወረርሺን ለመታደግ ቢሆንም አሁንም በርካታ ሕፃናት በየሰፈሩ ተጠጋግተው ሲጫወቱ እየተስተዋለ ነው። ለጥንቃቄ ሲባል በየተቋማቱ የተቀመጡ የነጽሕና መጠቢቂያዎችን ላለመጠቀም የሚያንገራግሩና ከፍ ሲልም ለግጭት የሚነሳሱ ግለሰቦች እንዳሉም በብዙ ቦታዎች ታይቷል።
በአጠቃላይ ሲታይ በተለይም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በኅብረተሰቡ ዘንድ የሚደረጉ አንቅስቃሴዎች ኮሮና የጠፋና መፍትሔ የተገኘለት የሚያሰመስሉ ናቸው። ለማናችንም ግልጽ መሆን ያለበት የቫይረሱ መተለላፊያ መንገድ እጅግ አደገኛ መሆኑ ነው። እጃችን፣ ልብሳችን፣ ጫማችንና የምንጠቀምባቸው መገልገያዎች ሁሉ ቫይረሱን አቆይተው ወደሌላው ለማስተላፍ እጅጉን ምቹ ናቸው። ከዚህም በላይ ከለይቶ ማቆያ ውጪ ከሆኑ ግለሰቦች አንድ ሰው እንኳ ተያዘ ማለት እጅግ በርካታ ሰዎች በቫይረሱ የመበከል ሁኔታው ከፍተኛ ነው። ስለሆነም በዚህ ሁኔታ ውስጥ መዘናጋት ማለት በራስ ላይ እሳት መለኮስ መሆኑን ደግመን ደጋግመን ልናጤነውና አስፈላጊውን የጥንቃቄ ዕርምጃ ሁሉ ያለምንም መዘናጋት ልንተገብር ይገባል!
አዲስ ዘመን ሚያዝያ 29/2012
እንጠንቀቅ ኮሮና አሁንም ቅርባችን ነው!