የዛሬዋ ቀን፣ ሚያዝያ 27 ለኢትዮጵያውያን ታላቅ ቀን ነች! አባቶቻችን በታላቅ ተጋድሎና በብዙ የህይወት መስዋእትነት ሀገራዊ ነፃነታችን እና ሀገራዊ የዜግነት ክብራችንን መልሰው በእጃችን ያስገቡበት፤ እንደቀደመው ዘመን ስለ ነፃነት ዋጋ ከፍለው ለነፃነት ዋጋ መክፈል ክብር መሆኑን ያደሱበት ዕለት ነውና። የአልገዛም፤ የአልደፈርም ባይነት፤ መኖር ከነፃነት ውጪ ትርጉም እንደሌለው በተግባር በህይወት መስዋእትነት ያስመሰከሩበት ጭምር ነው።
ከዳር እስከ ዳር ፤ከሰሜን አስከ ደቡብ ፤ ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ፤ ስለነፃነት በዱር በገደሉ፣ በብዙ ረሀብ፣ በብዙ ጥማት፣ በብዙ መታረዝና በብዙ የደም መስዋዕት በሚታደስ ታልቅ ተስፋ፤ በብዙ ጽናት ታግለው የትግሉ ፍሬ የሆነውን ነፃነታቸውን በስሜት ሲቃ ውስጥ ሆነው የተቀዳጁበት ቀን ነች፤ የዛሬዋ ቀን!
ኢትዮጵያዊነት ከነፃነት ትግል ጋር ያልተሳሰረ ዘመን ባይኖረውም ያ ትውልድ ቀደም የነበረውን የነፃነት የተጋድሎ ታሪክ በአዲስ የአልገዛም ባይነት ታሪክ ማደስ የቻለ ነው። ከቀደመው የነፃነት ትግል የሚለየው በተከፈለው መስዋእትነት ክብደት ሳይሆን የአልገዛም ባይነቱ መንፈስ ልእልና አግኝቶ የወደቀን
ባንዲራ የማንሳት ፣ የወደቀን የህዝብ መንፈስ የማደስ፣ በህይወት የመዋጀት የተጋድሎ ታሪክ መሆኑ ነው።
ተጋድሎው ኢትዮጵያውያን ስለነፃነት ያላቸውን ቀናኢነት በህይወታቸው መዋጀት የቻሉ ጀግኖችን ማፍራት ያስቻለ ትልቅ ታሪካዊ ቀን ነው። እነዚህ በታሪክ ውስጥ የተንሰላሰሉ የነፃነት የተጋድሎ ታሪኮች ስለነፃነት ተጋድሎ የሚታማና ለወቀሳ የሚዳረግ ትውልድ እንደሌለ አመላካቾች ናቸው።
ችግራችን ግን እያንዳንዱ ዜጋ ለሀገሩ ነፃነትና ለባንዲራው ክብር ህይወቱን መስዋእት አድርጎ ለመስጠት ያለውን ቁርጠኝነት ያህል ዴሞክራያዊ ስርዓት በመገንባት የነፃነቱን ተጋድሎ ሙሉ ማድረግ አለመቻላችን ነው።
ነፃነት በራሱ ጥልቅ ማህበራዊ እሴት መሆኑ በየትኛውም ዘመን ለጥያቄ ባይቀርብም ነፃነት አልፋና ኦሜጋ /ሙሉ/ የሚሆነው ነፃነቱ የሚፈጥረውን ሁለንተናዊ ማህበራሰባዊ ተጠቃሚነትን እውን ማድረግ ሲያስችል ነው። ይህ ደግሞ እንደ ነፃነት ትግሉ ማህበረሰባዊ ዝግጁነትና ቁርጠኝነት የሚጠይቅ ነው። ከዚህ ውጪ ያለው እውነታ የነፃነትን ትርጉም ሊቀጭባቸው የሚችል ማህበራዊ ነቀርሳ ነው።
ነፃነትን በምሉእነቱ ማጣጣም የሚገደድ ፤ ለዚህ
እውነታ የተገዛ ትውልድ ሲመጣ ድንገትም ለነፃነትና ለነፃነት ተብሎ የተከፈለው ተጋድሎ ሊያንስበት የተጋድሎው ሙሉ ትርጉም ሊጠፋው ይችላል። ይህንን ነፃነት አልፋና ኦሜጋ አድርጎ በትውልዶች ለማሻገር አሁን ያለው ትውልድ ትልቅ ኃላፊነት ተጥሎበታል። ከዚህ አንጻር የዛሬዋን የድል ቀን አድርገን ስንዘክር የቀደሙት አባቶቻችን የከፈሉትን ዋጋ ሙሉ ለማድረግ የነፃነት አስተሳሰባችንን ከሀገር ሉአላዊነት ባለፈ ዴሞክራሲያዊ ሀገር ወደ መገንባት የተጋድሎ ታሪክ ልናሻግረው ይገባል።
ዛሬ ላይ እኛ ያለፈው ትውልድ ስለ ሀገር ነፃነት የከፈለውን ተጋድሎ እንደም ንዘክረው ሁሉ መጪው ትውልድ የነፃነቱን የተጋድሎ ታሪክ አልፋና ኦሜጋ በማድረጋችን ሊዘክረን ይገባል። ለዚህ ደግሞ ራሳችንን የእውነተኛ ዴሞክራሲዊ ስርዓት ግንባታ ሀዋሪያ አድርገን ማቅረብ ይጠበቅብናል።
የዚህ ዘመን ትውልድ የተጋድሎ ታሪክ ምሰሶው ደም ሳይሆን የሌላውን ዜጋ ሰብዓዊና ፖለቲካዊ ነፃነት በአግባቡ ተረድቶ ስለራሱና ስለሌላው ዜጋ መብት ራስን መስዋአት አድርጎ ማቅረብ ነው። ይህ ደግሞ ብዙ ፉከራና ቀረርቶ የሚፈልግ ሳይሆን፤ ከሁሉም በላይ ከራስ ጋር መታረቅን የሚጠይቅ ነው።
አሜሪካውያን የቀደመውን ትውልድ አብዝተው የሚያወድሱት ከውጭ ጠላት ጋር ባደረጓቸው ጦርነቶች /ካሉ/ ባስገኘላቸው ድል፤ ወይም በእርስ በርስ ጦርነቱ ወቅት በተፈጠሩ ጀግኖች ሳይሆን ዘመን ተሻጋሪ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ባለቤቶች ስላደረጓቸው፤ ይህም ዓለም አቀፋዊ መገለጫቸው በመሆኑ ነው።
እኛም በየዘመኑ የህይወት ዋጋ እየከፈለ ነፃነታችንን አስጠብቆ የቆየ ትውልድ ልጆች በመሆናችን የአባቶቻችንን የተጋድሎ ታሪክ እያሰብን መዘከራችን ከተከፈለልን ዋጋ አንጻር በጣም ትንሽ በሚባል የዋጋ ስልት የሚሰላ ነው። ከዚህ የበለጠው ግን አባቶች በብዙ የህይወት መስዋዕትነትና ዋጋ ያስረከቡንን ነፃነት አልፋና ኦሜጋ ወደሚያደርገው የዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ምሉእ ታሪክ ስናሻግረው ነው።
ለዚህ ደግሞ የተጀመረውን የለውጥ መንገድ በቀደመው ዘመን የተጣመመ የፖለቲካ መንገድ ከፈጠረው እስትንፋግ አንጎበር ወጥተን ለራሳችንና ለመጪው ትውልድ በሚጠቅም መልኩ ፤ከሁሉም በላይ ደግሞ አባቶቻችን በብዙ ተጋድሎ ያስረከቡንን ሀገራዊ ነፃነት ወደ ሁለንተናዊ ማህበረሰባዊ ነፃነት ልናሳድገው ይገባል። ይህ ደግሞ ትውልዱ በራሱ ጊዜ ሊያከናውነው የሚገባ ታሪካዊ ኃላፊነት ጭምር ነው። የዛሬዋንም ቀን ስናከብር በዚህ መንፈስና ኃላፊነት ውስጥ ሆነን ሊሆን ይገባል።
በአባቶቻችን የተጋድሎ የድል ቀን ላይ ሆነን!