አዳዲስ ቁሳቁስ፣ የንድፍ አቀራረቦች እንዲሁም በዲጂታል ቴክኖሎጂ እና በትላልቅ ግንባታዎች ውስጥ ያሉ መሻሻሎች በግንባታ ኢንዱስትሪ ውስጥ ፈጣን ለውጥን እያመጡ ነው። ፈጣን መንገዶችንና ኃይል ቆጣቢ መኖሪያዎችን ማስተዋወቅ ግንባታዎችን ለማቀላጠፍ አስፈላጊ ነው። ሁልጊዜ አዳዲስ የፈጠራ መሣሪያዎች እና ቴክኒኮች በመታየት ላይ ሲሆኑ፣ ዛሬ በሲቪል ምህንድስና ውስጥ ጥቅም ላይ የዋለው የአዳዲስ ቴክኖሎጂ ለውጦች እየተበራከቱም ይገኛሉ። ከመጡ እድገቶች ውስጥ የተወሰኑትን እንመልከት።
እራስን በራስ መድፈን
ሲሚንቶ በግንባታ ውስጥ በሰፊው ጥቅም ላይ ከሚውሉ ግብዓት ውስጥ አንዱ ነው። ነገር ግን ወደ ሰባት ከመቶው አመታዊ የአየር ብክለት ከሚያደርሱት ውስጥ ይመደባል። የህንፃ መሰንጠቅ በግንባታ ውስጥ ትልቅ ችግር ተደርጎ ይወሰዳል። አብዛኛውን ጊዜ በውሃ እና ኬሚካሎች ምክንያት ይከሰታል። የባዝ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች የህንፃ መሰንጠቆች ሲፈጠሩ እራሳቸውን የሚደፍኑበት ቴክኖሎጂ እያስተዋወቁ ይገኛሉ። ቴክሎጂው ባክቴሪያን ከጥቃቅን እንክብሎች ጋር በማዋሀድ የሚከናወን ሲሆን፣ በስንጥቅ ግንባታዎች ላይ ውሃ ሰርጎ ሲገባ ጥቃቅን ድንጋዮችን እንዲመረቱ በማድረግ ስንጥቁ እርስ በርስ እየተጠባበቀ እንዲደፈን ያደርጋል።
የሙቀት ማገጃ
በግንባታ ኢንዱስትሪ ውስጥ አላስፈላጊ የሆኑ የግንባታ እቃዎች እየበዙ በመምጣታቸው ሙቀት እንዲፈጠር በር ከፍቷል። ሙቀት በቀጥታ በግድግዳዎች ውስጥ የሚያልፍ በመሆኑ አጠቃላይ ህንፃው በሙቀት የመታፈን እድል አለው። ህንፃዎች እንከን የለሽ እንዲሆኑ ለማድረግ አጋጅ ወይም ስቱዲዮ ፍሬም ይዘጋጃል። በተጨማሪም እንደ ደረቅ ግድግዳ ወደ ውስጣዊ ፋሺያ ያለው ግድግዳ በግንባታ ወቅት ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል። ይህ ሂደት የሙቀት ማገጃ በመባል ይታወቃል። ኤሮጌል የሚባለው ቴክኖሎጂ የተሰራው በናሳ ክራይጄኒክ ኢንስቲትዩሽን ሲሆን፣ ቴክኖሎጂው
እጅግ በጣም ውጤታማ ከሆኑት የሙቀት አማቂ ቁሳቁስ አንዱ ተደርጎ ይወሰዳል። አሜሪካ ይህን ቴክኖሎጂ የፋይበር ግላስን ተክቶ አገልግሎት ላይ እንዲውል አድርጋለች።
የፎቶቫልታይክ ግላስ – ሙጫ
በሲቪል ኢንጂነሪንግ ውስጥ ጥቅም ላይ ከሚውሉት እጅግ በጣም አዲስ ከሆኑት ቴክኖሎጂዎች ውስጥ አንዱ የተቀናጀ የፎቶቫልታይክ (ቢአይቪ) ሙጫ ግንባታ ነው። ይህም አጠቃላዩን የህንፃ ክፍል ወደ ፀሐይ በማዞር የሚከናወን ነው። እንደ ፖሊሶላር ያሉ ኩባንያዎች መዋቅራዊ የግንባታ ቁሳቁስ፣ መስኮቶችን፣ መጋዘኖችን እና ጣሪያዎችን በፎቶቫልታይክ መስታወት ይሰራሉ። የፖሊ ሶላር ቴክኖሎጂ ትይዩ የሆኑ ግድግዳዎች ከፍተኛ ሀይል በማመንጨት ረገድ ቀልጣፋ ናቸው። ይህ ማለት ህንፃው በቀጥታ ወይንም በጎን በኩል በመሸፈን ሊሰራ ይችላል። እንዲሁም ለኃይል የሚወጡ ሂሳቦችን መቆጠብ ያስችላል።
የኬኒቲክ የእግረኛ መንገድ
ግንባታ ላይ ካሉ የቅርብ ጊዜዎቹ የሲቪል ምህንድስና ቴክኖሎጂዎች ውስጥ አንዱ የኬይኔቲክ ኃይል ነው። የመንገድ ወለሎች የእግሮችን ኃይል እንዲጠቀሙ የሚያስችል ቴክኖሎጂ ነው። በከፍተኛ የትራፊክ ቦታዎች ውስጥ በቤት ውስጥ ወይም ከቤት ውጭ ሊያገለግል ይችላል። እናም ኤሌክትሮማግኔቲክ ወደ ውስጥ የማስገባት ሂደት በመፍጠር በራሪ ኃይል ማከማቸት ይችላል። ቴክኖሎጂው ብዙ የሰዎች ፍሰት የሚኖርበት የትራንስፖርት ማዕከላት አካባቢ በተሻለ ተመራጭ ያደርገዋል። እስካሁን ድረስ ኩባንያው ያከናወነው ትልቁ ተልእኮ በሪዮ ዲ ጄኔሮ ውስጥ በእግር ኳስ ሜዳ ላይ የሚገኘውን የጎርፍ መጥለቅለቅ ለሀይል እንዲውል ማድረግ ነው። በተጨማሪም በአሁኑ ጊዜ ከለንደን ካናየር ዋልታ ጣቢያ የጎዳና ላይ መብራቶችን በዚሁ ቴክኖሎጂ አገልግሎት እንዲሰጡ እየተደረገ ነው።
የኬኔቲክ መንገድ
የጣሊያን ጅምር የከርሰ ምድር ኃይል ማመንጫ ጣቢያ በመንገዶች ውስጥ የኬኔቲክ-ሀይል አቅም እየመረመረ ነው። ተሽከርካሪዎችን ወደ ኤሌክትሪክ ኃይል በማዛወር የተፈጠረውን የኬኔቲክ ኃይል የሚቀይር ሊብራ የተባለ ጎማ መሰል ቴክኖሎጂ ፈጥሯል። በአገሪቱ በሚላን ከሚገኘው ፖሊቴክኒክ ዩኒቨርሲቲ ጋር በትብብር
የተሰራው ሊብራ የብሬኪንግ መኪና የኬኔቲክ-ኢነርጂ ኃይልን ይፈጠራል በሚል አገልግሎት ላይ ውሏል። ቴክኖሎጂው ኤሌክትሪክ ሀይል ከማስተላለፉ በፊት ኃይልን መሰብሰብ እና መለወጥ ይችላል። መሳሪያው የመንገድ ደህንነትን ከማሻሻል በተጨማሪ የመንገድ ትራፊክ ዘላቂነትን ያሻሽላል እንዲሁም ያበረታታል።
የትንበያ ሶፍትዌር (የኮምፒውተር ፕሮግራም)
የማንኛውም ህንፃ መዋቅራዊ አቋም ከግለሰባዊ ክፍሎች ጋር ተመሳሳይ ነው። እነዚህ የህንፃ ክፍሎች አንድ ላይ የሚጣመሩበት መንገድ በቁሳቁሶች ምርጫ እና የሚሰሩበት የተመረጠ ቦታ የሚወስነው ሲሆን፣ ሁሉም ነገሮች ህንፃው በመደበኛ ወይም በጣም በከፋ ሁኔታ እንዴት መከናወን እንደሚችል ማሳያ ናቸው። የደህንነት እና የመንግስት ደንቦችን በሚያከብር መልኩ ሲቪል መሐንዲሶች እጅግ በጣም ብዙ ቁርጥራጮችን ወደ ግንባታ ዲዛይኖች መለወጥ አለባቸው። ትንበያ ሶፍትዌሮች (የኮምፒውተር ፕሮግራም) በሲቪል ምህንድስና ውስጥ በጣም አዳዲስ መዋቅሮች እንኳን ሳይቀሩ ደህንነታቸው የተጠበቀ እና ቀልጣፋ መሆናቸውን ለማረጋገጥ ሊረዳ ይችላል። ለዚህ ምሳሌ የሚሆነው የውንብሌ ስታድየም ሲሆን፣ የቤኔት ማህበር ለግንባታው የትንበያ ሶፍትዌር በመጠቀም ልዩ የሆነ እግርኳስ መጫወቻ ሜዳ መስራት አስችሎታል።
3 ዲ ሞዴሊንግ
የፕላኒንግና የግንባታ ፈጠራዎች ማደግ የከተሞችን እድገት እየለወጠው ይገኛል። በሳይበር 3 ዲ ዘመናዊ የ 3 ዲ ህንፃ ሞዴሎችን በማምረት ረገድ የተካኑ የፈጠራ ባለሙያዎች እየተበራከቱ ይገኛሉ። በዚህም ዘመናዊ ህንፃዎች በብዛት እንዲገነቡ አድርጓል። 3 ዲ ህንፃዎች አርክቴክቸራል፣ ኢንጅሪንግንና የኮንስትራክሽን ዘርፉን ከሳይበር 3 ዲ ሶፍትዌር ጋር የተሳሰረ እንዲሆን ረድቶታል። ሞዴሉ ከ3ዲ ጂኦግራፊ መረጃ ሲስተሞች ያሉት ሲሆን፣ ለምሳሌ አውቶ ካድና ኢ.ኤስ.አር.አይ እንዲሁም የ3 ዲ የከተማ ህንፃዎች መረጃዎች ያሉት የ3 ዲ አርክቴክቸር ማሳያ ሶፍትዌርም ይጠቀማል። የ3 ዲ ሞዴሉ የከተሞች ግንባታ መረጃ፣ ስለ ሀይልና ዘላቂነት እና የንድፍ ዕቅድ ይይዛል።
አዲስ ዘመን ሚያዝያ 20/2012
መርድ ክፍሉ