
አዲስ አበባ፡- የግብጽ ውሳኔ ሰጪና ተደራዳሪ አካላት በሀሳብ ያለመገናኘት በግድቡ ዙሪያ በጋራ ተጠቃሚነት መርህ ከስምምነት ላይ እንዳይደርስ ማድረጉን የቀድሞ የህዳሴ ግድብ ተደራዳሪና የምስራቅ ናይል ቴክኒክ አህጉራዊ ጽ/ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ ፈቅአህመድ ነጋሽ ገለጹ። አቶ ፈቅ አህመድ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት፤ በግብጽ ውሳኔ ሰጪው ደህንነቱና የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ ሲሆን፤ የውሃ ጉዳይ ላይ የሚደራደረው ደግሞ የውሃ ሚኒስትሩ ነው። በዚህም በየጊዜው የሚደረገው ድርድር ሦስቱ አካላት የሚስማሙበት እንዳይሆን አድርጎታል። ከዚያ ተሻግሮም ሌሎች አካላት ጭምር በመካከል ገብተው አገራቱ ያልተገባ ውዥንብር ውስጥ
‹‹የግብጽ ውሳኔ ሰጪዎችና ተደራዳሪዎች በሀሳብ ያለመገናኘት የውሃ ድርድሩን ፈትኖታል›› – አቶ ፈቅ አህመድ ነጋሽ እንዲገቡም አስገድዷቸዋል። የኢትዮጵያ አቋም አንድ አይነትና ድርድሩም ሆነ ውሳኔው በውሃ ሚኒስትሩ የሚከናወን በመሆኑ ለድርድር በቀረቡ ቁጥር ብዙውን ጊዜ ሀሳቡ ተለዋዋጭ ሳይሆን ነው የቆየው።
እንደ አቶ ፈቅአህመድ ገለጻ፤ ኢትዮጵያ ውስጥ የውሃ ጉዳይ የውሃ ሚኒስትር ብቻ ነው። ውሳኔዎችም ከአገር ጥቅም ጋር ተያይዘው ይካሄዳሉ። ይህ ሲደረግ ደግሞ የሌሎችን ብሔራዊ ጥቅም በሚደፈጥጥ መልኩ አይደለም። የግብጽ ውሳኔ ግን ከዚህ የተለየና እኔ ብቻ ባለቤት ነኝ ባይነት የበዛበት ነው።
ይህም የውሃ ድርድርን መርህ ያልተከተለ ነው። ግብጽ በህገመንግስቷ አንቀጽ 44 ላይ ያስቀመጠችውም በጋራ ተጠቃሚነት ዙሪያ የማያምን ነው የሚሉት ዳይሬክተሩ፤ ‹‹የግብጽ መንግስት ግብጽ በናይል ላይ ያላትን ታሪካዊ መብት ይጠብቃል፤ ይከላከላልም›› የሚለው የፖለቲካ ውሳኔ የግድቡ ጉዳይ በስምምነት እንዳይቋጭና ወደ ሥራ እንዳይገባ እንዳደረገው አስረድተዋል።
ስምምነቱ በእስከዛሬው የ13 ዓመታት ድርድር ተቋጭቶ ቢሆን ኖሮ ሦስቱም አካላት በተለያየ መልኩ ጥቅማቸውን ያዩ እንደነበር የጠቅሱት ዳይሬክተሩ፤ በተለይም ግብጽ በአሰዋን ግድብ ምክንያት ከቦታ ቦታ የሚንከራተተውን ህዝቧን መታደግ ያልቻለችው በራሷ ተደራዳሪዎችና ውሳኔ ሰጪዎች ምክንያት እንደሆነ ገልጸዋል። የአሰዋን ግድብም በደለል ተሞልቶ ከአሁን አሁን ፈርሶ ስጋት ውስጥ ጣለኝ የሚለውን ፍራቻዋን መቀነስ ያልቻለችውም በዚህ ሳቢያ ነው ሲሉ አክለው ገልጸዋል።
አዲስ ዘመን መጋቢት 12 ቀን 2012 ዓ.ም
ጽጌረዳ ጫንያለው