አዲስ አበባ ከሚያዝያ 3-4/2011 የአፍሪካ ንግድና የፋይናንስ አለምአቀፍ ጉባኤን እንደምታስተናግድ የአዲስ አባባ ንግድና የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት አስታወቀ፡፡
ምክር ቤቱ ዛሬ ባካሄደው የንግድና የፋይናንስ ጉባኤ ላይ መዲናዋ የአፍሪካ ንግድና የፋይናንስ አለምአቀፍ ጉባኤ ልታስተናግድ መሆኗን ይፋ አድርጓል፡፡
ምክር ቤቱ ጋና ከሚገኘው ‘Rscue shiping and investment agency’ ጋር በመተባበር የመጀመርያው ዓለም አቀፍ የአፍሪካ ንግድና ፋይናንስ ጉባኤ በመዲናዋ የሚያካሂድ ሲሆን ኢትዮጵያን ጨምሮ በርካታ የአፍሪካ አገራትን የሚወክሉ የመንግሥት መሪዎችና ከፍተኛ ባለስልጣናት፣ የፖሊሲ አውጪዎች፣ የትልልቅ ኩባንያዎች ባለቤቶችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በአፍሪካ ህብረት አዳራሽ ይካሄዳል ተብሏል፡፡
የአዲስ አባባ ንግድና የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ወ/ሮ መሰንበት ሽንቁጤ እንደገለፁት በጉባኤው የተለያዩ ሀገራት የንግድና የፋይናንስ ፖሊሲዎችና ማናጅመንት ተሞክሮዎች ቀርበው ለፖሊሲ ግብአት የሚሆኑ አፈፃጸሞች ይዳሰሱበታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
የም/ቤቱ ዋና ፀሃፊ አቶ ጌታቸው ረጋሳ በበኩላቸው በዚህ ዓለም አቀፍ ጉባኤ የአፍሪካ ህብረት፣ የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን፣ የአፍሪካ ልማት ባንክ፣ የምዕራብ አፍሪካ መንግስታት የኢኮኖሚ ማህበረሰብ(ኢኮዋስ)፣ ሳዴክ፣ የአፍሪካ ንግድና ልማት ባንክ የመሳሰሉት ተቋማት ተገኝተው በአህጉሪቱ ለሚስተዋለው ዝቅተኛ የንግድ ትስስር መፍትሄዎች ይቃኛሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ገልፀዋል፡፡
በማዕረግ ገ/እግዚአብሀር