አዲስ አበባ፡- በኢትዮጵያ 50 በመቶ በሚሆኑት የጤና ተቋማት በህግ የተፈቀደውና ንጽህናው የጠበቀ የጽንስ ማቋረጥ ህክምና አገልግሎት እንደማይሰጡ ተገለጸ። የጤና ተቋማት ንጽህናው የጠበቀ የጽንስ ማቋረጥ የህክምና አገልግሎት አለመስጠታቸው እናቶችን እስከ ሞት ለሚያደርስ ውርጃ በር የሚከፍት መሆኑን የህክምና ባለሙያዎች አመለከቱ።
በፌዴራል ጤና ሚኒስቴር የእናቶች፣ ህጻናትና የስርዓተ ምግብ ዳይሬክተር ዶክተር መሰረት ዘላለም በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት በአሁን ጊዜ 50 በመቶ በሚሆኑት የጤና ተቋማት ንጽህናውን የጠበቀ የጽንስ መቋረጥ አገልግሎትን እየሰጡ እንደሚገኙ ገልጸው እኤአ በ2020 ሁሉም የጤና ተቋማት አገልግሎቱን እንዲሰጡ ስራዎች እየተሰሩ ይገኛሉ።
ጽንስ ማቋረጥ ህጋዊነቱን ጠብቆ እስከተሰራ ድረስ የትኛውም የጤና ተቋም ላይ አገልግሎቱን ማግኘት የእናቶች መብት መሆኑን የገለጹት ዶክተር መሰረት፤ የፌዴራል ጤና ሚኒስቴር የህክምና ባለሙያዎቹን ክህሎትና እውቀት ለማሳደግ እንዲሁም የባለሙያዎችን አመለካከት ለመቀየር ስልጠና እየተሰጠ መሆኑንም ጠቁመዋል።
ከዚህም ጎን ለጎን የህክምና መሳሪያዎችን ተደራሽ ለማድረግ ጥረት እየተደረገ መሆኑን የጠቆሙት ዶክተር መሰረት ይህን ተግባራዊ ለማድረግም የዘርፉ አመራሮች በየክልሎቹ በኃላፊነት መንፈስ እየሰሩ ናቸው ብለዋል።
በየካቲት 12 ሆስፒታል በድንገተኛና በቀጠሮ ህክምና ንጽህናውን የጠበቀ የጽንስ ማቋረጥ አገልግሎት እንደሚሰጥ የሚገልጹት የሆስፒታሉ የማህጸን፣ ጽንስና ተመላላሽ ህክምና ዳይሬክተር ዶክተር ሀብታሙ መንጌ፤ በአሁኑ ጊዜ በሆስፒታሉ ጽንስ የማቋረጥ አገልግሎትን ለመስጠት አልፎ አልፎ ከሚያጋጥም የመድሃኒቶች አቅርቦት መቆራረጥ በስተቀር በህክምና መሳሪያዎች ረገድ የጎላ ችግር አለመኖሩን ገልጸዋል።
እንደ ዶክተር ሀብታሙ ገለጻ፤ ከ2005 ዓ.ም በፊት እናቶች ጽንስ ማቋረጥ ይፈልጉና ሆስፒታሉ የተሟላ መሳሪያ ስላልነበረው አገልግሎቱን ለማግኝት ይቸገራሉ። በአሁኑ ጊዜ ግን በአዲስ አበባ በየትኛውም ሆስፒታልና ጤና ጣቢያዎች ንጽህናውን የጠበቀ የጽንስ ማቋረጥ አገልግሎት ይሰጣል። የመሳሪያና የመድሃኒት አቅርቦቱ የተሻለ በመሆኑ የተነሳም ንጽህናውን ባልጠበቀ ውርጃ ምክንያት ይሞቱ የነበሩ የእናቶችን ቁጥር ከ34 በመቶ ወደ 10 በመቶ ዝቅ ማድረግ ተችሏል።
አሁንም ድረስ ንጽህናውን ያልጠበቀ ውርጃ የሚካሄድባቸው ቦታዎች አሉ የሚሉት ዶክተር ሀብታሙ ሆስፒታሉ በድንገትም ሆነ በፕሮግራም የሚሰጠውን ንጽህናውን የጠበቀ ጽንስ ማቋረጥ ህክምና አገልግሎት ነፍሰጡር እናቶች በነጻ ያገኛሉ ብለዋል። አልፎ አልፎ የመድሃኒት እጥረት ሲያጋጥም መድሃኒት ግዙ ቢባሉም የአልጋ፣የላቨራቶሪና የመድሃኒት አገልግሎትን ያለምንም ክፍያ እንደሚያገኙና መድሃኒቱም በጣም ተወደደ ከተባለ ከ70 እስከ 100 ብር አይበልጥም ብለዋል።
በአገሪቱ ካሉት 50 በመቶ የሚሆኑ የጤና ተቋማት በህክምና መሳሪያዎች ችግር፣በሰው ሀይል እጥረትና ክሊኒኮቹ ለታካሚዎች ምቹ ባለመሆናቸው ምክንያት የጽንስ የማቋረጥ አገልግሎት እየሰጡ አለመሆናቸው ግን እናቶች ንጽህናው ወዳልተጠበቀ ጽንስ ማቋረጫ ቦታዎች እንዲሄዱ ያደርጋል ያሉት ዶክተር ሀብታሙ፤ በባለሙያ ያልተደገፉ የጽንስ ማቋረጥ ህክምናዎች ለእናቶች ጤና መቃወስና ሞት ምክንያት ይሆናል ብለዋል።
ንጸህናው ያልተጠበቀ ውርጃ አካሂደው የማህጸን ኢንፌክሽን፤ የልጁ ወይም የእንግዴ ልጁ ማህጸን ውስጥ መቅረት፣ የማህጸን መቀደድ፣ የአንጀት መጎዳት፣ወዘተ አጋጥሟቸው ወደ ሆስፒታሉ የሚመጡ እናቶች መኖራቸውን በአብነት አንስተዋል።
“አንድ እናት መሞት የለባትም” እያልን ንጽህናውን የጠበቀ የጽንስ ማቋረጥ አገልግሎት በሁሉም የጤና ተቋማት ማዳረስ ግድ እንደሚል የገለጹት ዶክተር ሀብታሙ መንግሥት በዚህ ጉዳይ ላይ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚኖርበት አስገንዝበዋል።
በቅዱስ ጴጥሮስ ሆስፒታል በህግ ለተፈቀደላቸውና አገልግሎቱን ማግኘት ለሚፈልጉ እናቶች ጽንስ የማቋረጥ አገልግሎት እንደሚሰጥ የተናገሩት በሆስፒታሉ የማህጸንና ጽንስ ህክምና ክፍል ኃላፊ ዶክተር ግርማ ደርቤ 50
በመቶ በሚሆኑት የሀገሪቱ የጤና ተቋማት ንጽህናውን የጠበቀ የጽንስ መቋረጥ አገልግሎት አለመሰጠቱ በእናቶች ጤና ላይ ብዙ አሉታዊ ጎኖች እንዳሉት አመልክተዋል።
ጽንስ ከሚቋረጥባቸው ምክንያቶች አንደኛው የጽንስ አፈጣጠር ችግር ሲሆን በተለይ በገጠር የጤና ተቋማት የባለሙያ እጥረትና እንደ አልትራሳውንድ ያሉ መሳሪያዎች እጥረት በመኖሩ ወደ ሆስፒታሉ ሪፈር ተጽፎላቸው የሚመጡ ነፍሰጡር እናቶች ስድስትና ሰባት ወራት አልፏቸው በመሆኑ ስነልቦናዊና የጤና መታወክና ህይወት ላይ አሉታዊ ጫና መኖሩን ጠቅሰዋል። እናቶች በጊዜው የጽንስ ማቋረጥ ህክምና አገልግሎቱን አግኝተው ቢሆን ኖሮ የጤና ጉዳት አያጋጥማቸውም ብለዋል።
“ሙያዊ ያልሆነ ውርጃን ለመከላከል ንጽህናው የጠበቀ ውርጃን በሁሉም የጤና ተቋማት ተደራሽ ማድረግ አንዱ መንገድ መሆኑን የጠቆሙት ዶክተር ግርማ፣ በኢኮኖሚ ዝግጁ ያለመሆን ተከትሎ የሚደረግ ውርጃን ለመከላከል የቤተሰብ ምጣኔ ላይ ብዙ ስራዎች መሰራት እንዳለባቸው ተናግረዋል።
በሆስፒታሉ አልፎ አልፎ የመድሃኒት መቆራረጥ ችግርና የመሳሪያ እጥረት ቢኖርም ባሉት የህክምና መሳሪያዎች፣ ባለሙያዎችና መድሃኒቶች በወር በአማካይ ከ10 እስከ 20 የሚደርሱ እናቶች አገልግሎቱን እያገኙ እንደሆነ ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ ውስጥ በአሁኑ ጊዜ ባለው የህክምና መሳሪያዎች ቴክኖሎጂ ምክንያት ጽንስ ማቋረጥ የህክምና አግልግሎት የሚሰጠው የጽንሱ ዕድሜ 28 ሳምንትና ክብደቱ ደግሞ ከአንድ ኪሎ ግራም በታች መሆኑን ማረጋገጥ ይገባል ብለዋል። ከዚህም ባሻገር ጽንስ የሚቋረጠው፣ በየጤና ተቋማቱ ንጽህናውን የጠበቀ የጽንስ ማቋረጥ የህክምና አገልግሎት የሚሰጠው ልጆች ኖሯቸው ተጨማሪ ልጅ ለማሳደግ ለማይችሉ፤ ባለማግባታቸው ምክንያት ልጅ ብቻቸውን ማሳደግ ለማይፈልጉ፤ ከባለቤታቸው ጋር በሚፈጠሩ ችግሮች ምክንያት፤ በጽንሱ ላይ የአፈጣጠር ችግር እንዳለ ከታወቀ፤ እርግዝናው ለጤናቸውም ሆነ ለህይወታቸው አደገኛ ከሆነና እርግዝናው የመጣው በአስገድዶ መደፈር ከሆነ መሆኑን የጤና ባለሙያዎች ይገልጻሉ።
አዲስ ዘመን ጥር 15/2012
Зовем открыть захватывающую вселенную фильмов превосходного качества онлайн – непревзойденный онлайн видеосервис.
Наслаждаться кинолентами в интернете прекрасное решение в 2024
году. Фильмы онлайн высоком
качестве три метра над уровнем неба 3 кинокрад