አዲስ አበባ፡- በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች አጋጥ መው የነበሩ የሰላም ማጣት ችግሮችን መቆጣጠር በመቻሉ አሁን አብዛኞቹ ወደ ተለመደ የመማር ማስተማር ሥራ መግባታቸውን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።
የሚኒስቴሩ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ደቻሳ ጉርሙ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት፤ በየዩኒቨርሲቲዎቹ ተማሪዎች እንዲነ ጋገሩና እንዲተማመኑ በማድረግ ለማግባባት በተ ሰራው ሥራ ተማሪዎች ተለቃቅሰው፣ ይቅርታ ተባብለው እና ታርቀው አብዛኞቹ ወደ ትምህርት እየተመለሱ ናቸው።
መቱ ዩኒቨርሲቲ የተወሰኑ ተማሪዎች ወደ መተኛ (ዶርም) አንመለስም በማለት ፈቃደኛ አለመሆናቸውን ጠቁመው፤ መቱ፣ ኦዳቡልቱ፣ ደብረታቦር እና እንጂባራ ላይ ተማሪዎች በህብረት ተሰብስበው ተመግበው ወደ ክፍል እና ወደ መተኛ ክፍል አንገባም ብለው ያስቸገሩበት ሁኔታ እንደነበር ተናግረዋል። ይህን ችግር ለማቃለል የልጆቹን መተኛ (ዶርም) በማቀያየር የተሻለ ሰላም እንዲሰማቸው እየተደረገ መሆኑን ጠቁመዋል።
በቅርቡ ችግር በተከሰተባቸው ዩኒቨርሲቲዎች ላይም ውይይት እየተካሄደ መሆኑን ጠቁመው፤የመዳ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችም በተደጋጋሚ የአገር ሽማግሌዎች ካነጋገሩዋቸው በኋላ ከትናንት በስቲያ በመታረቅ ወደ መማር እንገባለን ማለታቸውን ተናግረዋል። ወደ ኋላ የቀሩት ዩኒቨርሲቲዎች በሁለት ቀን ውስጥ ወደ መደበኛ የመማር ማስተማር ሥራ ይገባሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ አመልክተዋል። በዩኒቨርሲቲዎች አካባቢ ያለው የማህበረሰብ ክፍል የሃይማኖት አባቶችን ጨምሮ እናቶች ሳይቀሩ ተማሪዎችን ለማረጋጋት ጥረት ማድረጋቸውን ተናግረዋል።
የአገር ሽማግሌዎችም ሰላምን ለመፍጠርና ለማረጋጋት ጥረት እያደረጉ መሆኑን ጠቁመው፤ በዚህም አብዛኞቹ ችግሮቻቸውን እያቃለሉ ሲሆን፤ የተወሰኑና ብዙ ተማሪዎች የቀሩባቸው ዩኒቨርሲቲዎችም ትምህርት በመጀመራቸው እርምጃ የሚያስወስድ ጉዳይ አለመኖሩን አመልክተዋል።
አዲስ ዘመን ህዳር 12/2012
ምህረት ሞገስ
Kidd, Li Li Joel T cialis with priligy Hypertension may be seen in non infectious causes that affect the kidneys