የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት የኢ-ኮሜርስ ማዕከል ኢትዮጵያ ውስጥ ሊገነባ ነው፡፡
ቀድሞ የምስራቅ አፍሪካ የኢ-ኮሜርስ ማዕከል ኬንያ ናይሮቢ ሊገነባ ታቅዶ የነበረ ሲሆን ኢትዮጵያ በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ መስክ እያሳየችው ባለው የተሻለ እንቅስቃሴና መንግስት በሰጠው ልዩ ትኩረት አዲስ አበባ ውስጥ እንዲገነባ ተወስኗል፡፡
በአፍሪካ ውስጥ 4 ኢ-ኮሜርስ ማዕከላት የሚገነቡ ሲሆን የምስራቅ አፍሪካው ማዕከል አዲስ አበባ ይገነባል፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ተለያዩ ሀገራት የሚያደረገው በረራ መበራከት፤ ኢትዮጵያ በቴክሎጂ እያደገች መምጣቷ እና መንግስት ለዘርፉ የሰጠው ትኩረት ኢትዮጵያ እንድትመረጥ አድርጓታል፡፡
ማዕከሉ ኢትዮጵያ ውስጥ በሚገነባበት ሁኔታ ዙሪያ የኢኖቬሽንና ቴክሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ጌታሁን መኩሪያ (ዶ/ር ኢንጂ.) ከአለም አቀፍ ፖሰታል ዩኒየን ዳይሬክተር ጀነራል አምባሳደር ቢሻር ሁሴን ጋር መክረዋል፡፡
ሚኒስትሩ ለማዕከሉ ግንባታ የሚስፈልገው የቦታ መረጣም ሆነ መስረት ልማት በፍጥነት እንሚሟላ አረጋግጠዋል፡፡
የማዕከሉ ኢትዮጵያ ውስጥ መገንባት ለ100ሺዎች የሥራ እድል እንደሚፈጥርና በኢትዮጵያ ውስጥ ከፍተኛ የገንዘብ ፍሰት እንዲኖር እንደሚያስችል ታምኖበታል፡፡
እንደ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ማዕከሉ የአፍሪካ ምርቶች ለማንኛውም ሀገራት እንዲታዩ በማድረግ ገበያውን እንዲቀላቀሉ ያግዛል፡፡