ሞዴል የገጠር መንደሮች ግንባታ ተጀመረ

ሲንቢጣ ቀበሌ ፦ የገጠሩን ማህበረሰብ አኗኗር ለማሻሻል የተጀመረው የገጠር ኮሪዶር በሁሉም አካባቢዎች እየተስፋፋ ነው። ትላንት ( ሰኞ ግንቦት 25) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሀላባ ዞን ዌራ ዲጆ ወረዳ ሲንቢጣ ቀበሌ የገጠር ኮሪዶር ልማት አካል የሆኑ ሞዴል የገጠር መንደሮች ግንባታን አስጀምረናል። ሞዴል የገጠር መንደሮቹ ቀላል ወጪ የሚጠይቁና በአካባቢው በሚገኙ ግብዓቶች የሚገነቡ ሲሆኑ አርሶ አደሩም ጤናማና ክብር ያለው ሕይወት እንዲኖር የሚያስችሉ ናቸው።
በአካባቢው ከ2 ሺህ ሄክታር መሬት በላይ በመስኖ የበቆሎ ምርጥ ዘር ብዜት እንዲሁም የአትክልትና ፍራፍሬ ልማት እየተካሄደ ሲሆን ከዚህ ቀደም በጎርፍና ድርቅ አደጋ ይታወቅ የነበረውን አካባቢ የልማት ተምሳሌት ያደርገዋል።
/ ምንጭ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ማህበራዊ ድረ ገጽ /

አዲስ ዘመን ማክሰኞ ግንቦት 26 ቀን 2017 ዓ.ም

Recommended For You