
አዲስ አበባ፡- አንጋፋው የማሲንቆና በገና ተጫዋች፣ ድምጻዊና የሙዚቃ መምህር አለማየሁ ፋንታ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።
ግጥምና ዜማ በመድረስና ክራር በመጫወት የሚታወቁት አለማየሁ ፋንታ፤ ለበርካታ ዓመታት በያሬድ የሙዚቃ ትምህርት ቤት በመምህርነት አገልግለዋል።
በተለየ የማሲንቆ አጨዋወታቸው የሚታወቁ ሲሆን፤ በዓለም ዙሪያ የኢትዮጵያን ባህል ማስተዋወቅ ችለዋል።
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የያሬድ ሙዚቃ ትምህርት ቤት የአለማየሁ ፋንታን ህልፈት አስመልክቶ ባስተላለፈው የኀዘን መግለጫ መልዕክት፤ ለኢትዮጵያ የሙዚቃ ማህበረሰብና ለመላው ሕዝብ ከባድ ኀዘን ነው ብሏል።
በዛሬው ዕለት የአስክሬን ሽኝት መርሐ-ግብር ተደርጎ የቀብር ሥነ ሥርዓት እንደሚፈጸምም ተገልጿል።
በጋዜጣው ሪፖርተር
አዲስ ዘመን ረቡዕ መጋቢት 3 ቀን 2017 ዓ.ም