«ህልሜን እየኖርኩት ነው» -የሺአለም ዋለ

“አዲስ አበባ በመጣን ሰሞን ነው፤ የጀርመን ቤተክርስቲያን ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር በነበረው ማሰር ሻፈርድ አስተባባሪነት የፈረንጆች የገና በዓል ሲከበር ዓይነ ስውራን የሙዚቃ ድግስ አዘጋጀን፤ ያን ጊዜ ታዲያ ያቀረበው የባህል ዘፈን በሙዚቃው ዘርፍ ትልቅ ደረጃ እንደሚደርስ ጠቁሞኝ ነበር” ይላል አርቲስት ተሾመ አሰግድ ስለ የሺአለም ምስክርነቱን ሲሰጥ፡፡

የግጥምና ዜማ ደራሲው ሙሉ ገበየሁ ደግሞ ይህን አለ፡፡ “ዛሬ ላይ የልብ ወዳጆች ስንሆን ገና በተዋወቅን ቀን እምቅ ችሎታው አስደንቆኝ አቅሜ በፈቀደው መጠን ላግዘው ለራሴ ቃል ገባሁ፤ በሰርግ ሥራዎች ይሁን በሌሎች መድረኮች ከጎኔ ለይቼው አላውቅም፡፡ የዮዲት ዘለቀን “ህልም አለኝ” የተሰኘ አልበሟን ሳዘጋጅ በቅንብር እንዲሳተፍ አድርጊያለሁ፡፡ የሺአለም ዋለ ማለት በአካል ጉዳተኝነቱ ሳይሸማቀቅ ያለውን ተሰጦ ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ ለማሳየት የሚጥርና ለሌሎች አካል ጉዳተኞች ምሳሌ መሆን የሚችል ነው” ይላል አርቲስት ሙሉ ገበየሁ ጥንካሬውን ለመናገር ቃል እያጠረው፡፡

የቶቶት ባህል ምግብ ቤት ሱፐርቫይዘር አቶ ተክሉ ጥላሁን በበኩላቸው “የቤታችን ድምቀት የመድረካችን ጌጥ ነው” ሲሉ ያሞካሹታል፡፡

“ተጫዋችና ተግባቢ በመሆኑ ፍቅር ባለዘበው አንደበቱ ስለአካል ጉዳተኞች ያለን ግንዛቤ የበለጠ እንዲሻሻል አስተምሮናል፤ ከዚህም የተነሳ መድረኩ ለአካል ጉዳተኞች የተመቸ አድርገን ሰርተናል፡፡ ይህን የተመለከቱ ታዳሚያንም ለእሱ ብቻ ሳይሆን ለእኛም ብርታት ሆነውናል” አሉ ሀሳባቸውን ሲገልፁ፡፡

“ለሙያው ያለውን ፍቅር በተግባር የሚገልጥና ለሌሎች እውቀቱን ለማካፈል የማይሰስት እንዲሁም ሰርቶ የማይደክመው ታታሪ ሙያተኛችን ነው” በማለት ምስክርነታቸውን የሰጡን ደግሞ የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ባህል ቱሪዝም ጽህፈት ቤት የኪነ-ጥበብ ኢንዱስትሪ ተቋማት ማበልፀግና ማስፋፋት የቡድን መሪ አለምፀሀይ ማሞ ናቸው፡፡

በዛሬው የልዩ ልዩ አምድ ላይ የዚህ ፅሁፍ አዘጋጅ፤ በሌለው ነገር ከመቆዘም ይልቅ ያለውን ፀጋ በማጉላት ዓይነ-ስውርነቱ የቸረውን ጥሞና በሙዚቃው የገለጠና ለብዙዎች የፅናት ምሳሌ የሆነውን የሺአለም ዋለ መከተን ልምድና ተሞክሮ ሊያስቃኛችሁ ወድዷል፡፡

53 ዓመታትን ወደኋላ

በ1964 ዓ.ም በምስራቅ ጎጃም ዞን መርጦለማርያም ይዳይ ቀበሌ የሺአለም ዋለ ተወለደ፤ ገና በተወለደ በ11 ወሩ እይታው በኩፍኝ ሲሰናከል ወደ ህክምና ከመውሰድ ይልቅ በየጠንቋይ ቤቱ አንከራተቱት፤ይሁን እንጂ እይታውን መታደግ አልቻሉም፡፡ ከዚህ በላይ ህይወቱን ያከፋው እናስተምረዋለን ብለው ከአዲስ አበባ ለዘመድ ጥየቃ የመጡ የአካባቢው ሰዎች ፊደል ያልቆጠሩ ወላጆቹን አታለው ከወሰዱት በኋላ የአዲስ አበባ ጎዳናዎች ላይ ለልመና አስቀመጡት፡፡

ምስጋና ለአማረ አስፋው ይግባውና በጊዜው የኢትዮጲያ ዓይነ-ስውራን ብሄራዊ ማህበር ሊቀመንበር የነበሩት አቶ አማረ አስፋው ከፀጥታ አካላት ጋር ቅንጅት በመፍጠር ለልመና የተጠቀሙበትን ግለሰቦች ለሕግ በማቅረብ በ1972 ዓ.ም የሺአለምን በባኮ ዓይነ-ስውራን አዳሪ ትምህርት ቤት በማስገባት ከጨለማ ወደ ብርሀን አሸጋገሩት፡፡ በአዳሪ ትምህርት ቤቱ አጋዥነት የሙዚቃ ተሰጦው የፈካለት የሺአለም በአውራጃ ደረጃ ለተካሄደው የሙዚቃ ፌስቲቫል ባኮ ወረዳ እንዲያሸንፍ አስተዋጽኦው ቀላል አልነበረም፡፡

ከትምህርቱና ከሙዚቃው ጎን ለጎንም የሙያ ስልጠና ወስዶ የተለያዩ እደ ጥበቦችን በመስራት አዳሪ ትምህርት ቤቱ በሚከፍለው ወርሀዊ ክፍያ ኪሱን ይደጉም ነበር፡፡ ይህ ችሎታው የ12ኛ ክፍል ውጤት በቀረበበት ወቅት ተደናግጦ ተስፋ እንዳይቆርጥ የሞራል ስንቅ ሆኖታል ፡፡ የነፍሱ ጥሪ ወደ ሙዚቃው አመዝኖ የተሻለ እድል ፍለጋ 1983 ዓ. ም የአዲስ አበባን መሬት ሲረግጥ የኢትዮጵያ ዓይነ-ስውራን ብሄራዊ ማህበር ያቋቋመው ወጋገን ባንድ ተቀበለው፡፡ የሺአለም እያንዳንዷን ቀን ሳያባክን በመጠቀሙ ጥረቱ ፍሬ አፍርቶ ተፈራ ነጋሽ፣ አሸብር በላይ፣ ዘውዱ በቀለና ማለፊያ ተካ ይሰሩበት የነበረው አታአ ባንድ እድል ሰጠው፡፡

የታዳሚው ሞራል የሙያ አጋሮቹ ድጋፍ አቅም ሆኖት በሙዚቃ እንጀራ ከመቁረስ ባለፈ ጎጆ ለመቀለስ በቃ።

ራማፎዛን ወቅሷል።

የደቡብ አፍሪካ የፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት ባወጣው መግለጫ ራማፎዛ ለኢላን መስክ ስልክ መደወላቸውን ገልጾ ‹‹ደቡብ አፍሪካ በሕገ-መንግሥት የጸና የሕግ የበላይነት እና ተጠያቂነት ያላት እንዲሁም ፍትህና እኩልነት የሰፈነባት ሀገር ናት›› ማለታቸውን በመግለጫቸው አስታውቀዋል።

ባሳለፍነው ወር ደቡብ አፍሪካ በፕሬዚዳንቷ በኩል ተፈጻሚ እንዲሆን ያወጀችው ረቂቅ የመሬት ሕግ ‹‹በአንዳንድ ሁኔታዎች መሬት ያለምንም የካሳ ክፍያ ሊወሰድ ይችላል›› የሚል አንቀጽ ነበረበት።የአሜሪካ መንግሥትም ከዚህ የፕሬዚዳንቱ አዋጅ በኋላ ተቃውሞውን አሰምቷል።አዲሱ የመሬት ሕግ መሬት ጥቅም ላይ እየዋለ ካልሆነ፣ ባለይዞታ ግለሰቦች ጥቅም ላይ ሊያውሉት ካልቻሉ እንዲሁም ለሕዝቡ አደጋ የሚሆን ከሆነ ምንም ካሳ ሳይከፈል የሚወሰድበትን አሠራር ይፋ ማድረጉን የደቡብ አፍሪካ የመሬት ሕግ  ቢሆንም ግን ምኞቱ ሙሉ አልሆነም ባለቤቱ እፁብ ድንቅ ሲሳይ ዳግም የሚባል ወንድ ልጅ ከሰጠችው በኋላ ህይወቷ በማለፉ የሙዚቃ ስራው ላይ ጥላውን አጠላበት፡፡ በወዳጆቹ ጉትጎታ ቤቱ እንዳይጎድል መምህርት ቦሰና ገብረ ዮሐንስ ጋር ዳግም በትዳር ተጣመረ፡፡ መምህርት ቦሰናም እያበረታችው አታአ ባንድ ተዘግቶ ሲበታተኑ ታምራት ደስታና ጌዲዮን ዳንኤል የሚሰሩበት ኪነ-ቤት ተቀላቀለ፡፡

ከኪነ-ቤት በኋላ ደግሞ ደብሊው 6 በሚባል ቤት ከብጻት ስዩም ጋር፣ ከሀይማኖት ግርማ ጋር እንዲሁ በአቦጊዳ የሰራ ሲሆን ይወዳል፣ ፋሲካ፣ ሺዋዘርፍና ሀበሻ ሪስቶራንት የሚሰኙት ከአጭር እስከ ረጅም ዓመት የሰራባቸው ቤቶች ናቸው። አሁን ላይ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ባህል ቱሪዝምና ኪነጥበብ ጽህፈት ቤት የኪቦርድ ባለሙያ ሆኖ እያገለገለ ሲሆን በትርፍ ጊዜውም በቶቶት ባህል ምግብ ቤት እየሰራ ይገኛል፡፡

በአንድ አጋጣሚ በቶቶት ባህል ምግብ ቤት የስራ ገበታው ላይ ሆኖ የአለማየሁ እሸቴን ሙዚቃ ሲጫወት አለማየሁ እሸቴ በቦታው ነበረና ደስ ተሰኝቶ ሸልሞታል ። ይህ ብቻም ሳይሆን ከጀማሪ እስከ አንጋፋ የሙዚቃ ሰዎች ጋር አብሮ የመስራት እድሉን አግኝቷል። ነገር ግን የመድረኮች አለመመቻቸት እንዲሁም የግንዛቤ እጥረቱ ሙሉ አቅሙን አውጥቶ እንዳያሳይ እንቅፋት ሆኖበታል። ይሁን እንጂ ከንፈር መጠጣ ሳይበግረው ነገ ጥሩ ይሆናል ብሎ በመጽናቱ በሙዚቃው ዘርፍ አሻራውን ለማሳረፍ ችሏል፡፡

ከዚህ ጋር ተያይዞ በአንድ ወቅት ለሰርግ ስራ ተዋውሎ በእለቱ የሙሽራው ወላጆች “ለቅሶ ድረሱ ብለን እድርተኛ አይደለም የጠራነው ሰርገኛ እንጂ” አሉ በብስጭት፡፡ ይህን ሲሰማ የሺአለም መሳሳታቸውን ከቃል ይልቅ በተግባር ሊያስተምራቸው ሽቶ ንግግራቸውን “ጆሮ ዳባ …” ብሎ ከሙዚቃ መሣሪያው ጋር መነጋገሩን ቀጠለ ፡፡ አላሳፈረውም አቧራው ጨሶ አለም ሲቀልጥ በዓይነ ስጋው እክል ሰበብ ውስጣዊ ችሎታውን የመዘኑት እኒያ የሙሽራው ቤተሰቦች ለይቅርታ እግሩ ስር ወደቁ፡፡

“እኔ የምደክመው የእለት እንጀራዬን ከማግኘት ባሻገር እልፍ የሺአለሞች እንዲበቅሉ ነው” ይላል ፍላጎቶን ሲገልጽ፡፡ ህልሙን እውን ለማድረግም መነሻ ለሆነው ለማህበሩ ወጋገን ባንድ አባላት በነፃ ሙያዊ ስልጠና እየሰጠ ይገኛል፡፡

ሀብታሙ ባንታየሁ

አዲስ ዘመን ሐሙስ ጥር 29 ቀን 2017 ዓ.ም

Recommended For You