“ኢትዮጵያ ለጎረቤት ሀገራት ጭምር የሚተርፍ የዲኤንኤ ምርመራ ተቋም ገንብታለች”  – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፡- ኢትዮጵያ ለጎረቤት ሀገራት ጭምር የሚተርፍ የዲኤንኤ ምርመራ ተቋም ገንብታለች ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡ የፌደራል ፖሊስ የፎረንሲክ ምርመራ እና ምርምር ልህቀት ማዕከልን ትናንት መርቀው ከፍተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት መልዕክት፥ ከአንድ ዓመት ተኩል በፊት እንደ ሀገር የዲኤንኤ ምርመራ ሲያስፈልግ ወደ ውጭ ይላክ እንደነበር አንስተዋል። ዛሬ ላይ ኢትዮጵያ ከዲኤንኤ ጋር የተያያዙ ችግሮች ሲገጥሟት በራሷ መሥራት ብቻ ሳይሆን የጎረቤት ሀገራት ጭምር ሊገለገሉበት የሚችል ተቋም መገንባቷን አስታውቀዋል።

ይህ በፀጥታ እና ደኅንነት ዘርፍ ባለፉት ዓመታት የሠራናቸው የሪፎርም ሥራዎች ውጤት ነው ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)።

አዲስ ዘመን ኅዳር 8 ቀን 2017 ዓ.ም

Recommended For You