ወሬው ሁሉ ከሙስናና ምዝበራ ጋር በተያያዘ የተጠረጠሩ በወንጀል የሚፈለጉ ሰዎች ስም ዝርዝር ነው፡፡ ከፖሊስ በወጣው መግለጫ የተጠርጣሪ ስሞች ተሰድረዋል፡፡ የባል ሚስት ልጆች ወንድሞች አክስቶች ጋብቻዎች የሩቅ የቅርብ ዘመድ ውሽሜ ሁሉም በሀብት ተንበሽብሸዋል፡፡ እንዲህ አይነቱ የተቀናጀ የተደራጀ ሕጻናቱን የማያውቁት ሚሊዮን ብር ባለቤት ያደረገ ዘረፋ ጉድ የሚያሰኝ ነው፡፡ የጉድም ጉድ፡፡ ሸማኔው ጊሀጌሎም ስጋ ቆራጩ ወርኬቦ፤ እማማ ይመናሹና አባባ ደቻሳም በሰሙት ነገር ግራ ተጋብተዋል፡፡ አንድ የጎረቤታቸው ልጅ የወጣውን የሰዎቹን ስም ዝርዝር ሲያነብላቸው ፈዘው ቀሩ፡፡
ሆሆይ ሀገሬ ጉድሽ አላልቅ አለ ምን በጀሽ ምንስሽ ተረፈ እንደው ምኑ ነው የቀራቸው? አሉ አዛውንቶቹ፡፡ ሁሉም በአንድ ድምጽ ሌብነትን አወገዙ፡፡ ሌባም ሌቦች፡፡ ሌብነትን ዘረፋን ተጸይፈው ድምጽ አሰሙ፡፡ ሌቦ ሌቦ ነይ የሚለውን ዘፈን ድሮ የዘፈነው ዘፋኝ ማን ነበር ሲሉ ጠየቁ፡፡ ዘመኑ ተፈትልኳል፡፡
ሌቦች እንደ ሰማዩ ጩሉሌ ሙጭልፊት ናቸው አሉ እማማ ይመናሹ፡፡ ከላይ አንዣቦ አንዣቦ ድንገት ጠልፎ እንደሚወስደው፡፡ እንደው የሰው ይቅር መቸም እንደሌለ ቆጥረውታል ሌላ ይቅር ምናለ እግዚአብሔርን ቢፈሩ ኖሮ አሉ ድምጻቸውን ጎላ አድርገው፡፡ ደሞ ብር ካለ በሰማይም መንገድ አለ የሚለው የድሮ ተረት ትዝ አላቸውና ብቻቸውን ሳቁ፡፡ ምን አሳቀሽ ይመናሽ ደቻሳ ጠየቁ፡፡ እንደው ከራሴ ጋር እያወራሁ ነው ደቻሳ ምንም የለም ሲሉ መለሱ፡፡
እግዜሩም እኮ የእኛ ነገር ግራ ሳያጋባው አይቀርም አሉ አባባ ደቻሳ፡፡ አንዱ ሲባል አንዱ፤ጉድ ጉድ ስንል ሌላ ጉድ የማያባራ ጉድ የሚታይባት፤ የሚሰማባት ሀገር ሆና አረፈች ብለው በዝምታ ተዋጡ፡፡
አባባ ደቻሳ ከዘራቸውን ደገፍ ብለው ሌቦች ሌብነት ጀግንነት ነው ያሸልማል የተባሉ ይመስላሉ እኮ እንዲህ ሀገር ማራቆት ነውርም አይደለም እንዴ? ሲሉ ጠየቁ፡፡ እግዜሩንም እኮ እንደ ሰው ንቀውታል፤ ምን ያመጣል እያሉ፡፡ አይ ደቻሳ ነገር የተበላሸው እኮ ሕዝቡ አምርሮ ወደ ፈጣሪ ያለቀሰባቸው ግዜ ነው፡፡ ወይ ፍረድ ወይ ውረድ እያለ እሪታውን ከከተማ እስከ ገጠር ሲያቀልጠው ሰምተህ አይተህስ የለም ወይ? አሏቸው፡፡ አዎ ልክ ነሽ ይመናሹ ከሕዝብ የተጣላ ከእግዜር የተጣላ ይባል የለ የሆነውም ይሄ ነው ሲሉ መለሱ፡፡
ባለፈው ሶስት ዓመት በድቅድቅ ክረምት ሕገወጥ ቤት ሰርታችኋል የተባሉ እንዲያም ሆኖ ግብር የመብራት የውኃ ሲከፍሉ የኖሩትን ሰዎች ርሕራሄ በሌለው፣ ጭካኔ በተሞላበት፣ ሰው በተኛበት በትራክተር ያፈረሱና እናት ሕጻን ልጇን እንደያዘች የተደረመሰባትን ስንቱ ያለቀበትን ታሪክ እዚሁ አዲስ አበባ አይተን ሰምተን አልቅሰን ምን አይነት ግዜ መጣ ብለን ነበር፡፡ መንግስት ዜጎቹን በጨለማው ክረምት ቤት ልቀቁ ብሎ ቤታቸውን አፈራርሶ የትም ውደቁ ሲል የዛ ሁሉ ድሀ እንባ ምን ያመጣል ብለው እኮ የማያስቡ ሰዎች ነበሩ አለ ሸማኔው ጊሀ ጌሎ፡፡ የበዛ ግፍ የግፍም ግፍ ነበር ሲፈጸም የነበረው፡፡ ይሄን መሰል ድርጊቶች ናቸው ክብሪት ሆነው ተለኩሰው ሌላ ሌላውም ተጨምሮ ሕዝቡን አስመርረው ዜግነቱን እስኪጠላ አድርሰውት የነበረው ሲሉ መምህር አበበ በረዥሙ ተነፈሱ፡፡
እነ ሌቦ ሌቦ ነይ በስማቸው ሀምሳ ሶስት ቤት እየያዙ በሚስትና ልጆቻቸው፤ በእቁባቶቻቸው፤ በወንድሞቻቸውና እህቶቻቸው፤ በአክስትና በአጎት ልጅ ጭምር መሬቱን ቤቱን ሲቀራመቱት በልማት ስም ባለቤትና ባለንብረቶችን እያፈናቀሉ ሲፈነጩ ኖሩ፡፡ እስቲ ምን ያልተዘረፈ ነገር አለ በዚች ሀገር የሚል ጉምጉምታ ከሁሉም ተሰማ፡፡
በየክፍለ ከተማው መሽጎ የነበረው የመሬት ይዞታ ሹምና ምንዝር ወሮበላ በመንግስት የተወረሱ የቀበሌ ቤቶችን ፋይል እያጠፉ በግለሰብ ስም እያዛወሩ፤ የሀሰት ካርታ እየሰሩ፤ ላሻቸው ሲሰጡ ሲሸጡ፤ ዜጎችን እያፈናቀሉ ትንሽ የካሳ ብር በመስጠት እነሱ በሚሊዮኖች ሲቸበችቡት፤ ሕዝቡ በድሕነት ማቅ ውስጥ እንዲኖር ሲፈረድበት፤ እነሌቦ በፎቅ ላይ ፎቅ፤ በሕንጻ ላይ ሕንጻ፤ በመኪና ላይ መኪና ሲደርቡ፤ይሄ ግፍ ይሄ ወጥ መርገጥ ምን ያመጣል? ብለው ማሰብ ይገባቸው ነበር አሉ አባባ ደቻሳ የመምህርን ንግግር ቀበል አድርገው፡፡ ቀን ሲያዘንብል እግዜሩም አብሮ መከፋቱን ፍርድ መስጠቱን ነው በእድሜያችን ያየነው፡፡ እነሌቦ ይሄም የገባቸው አይመስልም ሲሉ አከሉበት፡፡
እግዚኦ አንቺ ሀገር መጨረሻሽ ምን ይሆን የሚያሰኙ ብዙ የግፍ ታሪኮች፤ አይደረጉም ተብለው የሚገመቱ ግን ደግሞ የተደረጉ ብዙ ሺህ ተቆጥረው የማያልቁ ግፎች መሰራታቸውን ሕዝቡ በሰፊው ያውቃል፡፡ ጠላ ቤቱ፤ ጠጅ ቤቱ፣ ሰፈሩ፣ መንደሩ፣ ሁሉም ወሬው እኮ ይሄ ነው፡፡ ማታ ማታ መዝናኛ ቦታ የሚሰማውን ለማመን ይከብዳል አሉ ደቻሳ፡፡ ሌብነት ጎሳና ዘር የለውም፡፡ የአማራም፣ የትግሬም፣ የኦሮሞም፣ የደቡብም፣ የሶማሌም፣ የሀደሬም፣ የጉራጌም፣ በሁሉም ብሔሮች ብሔረሰቦች ውስጥ ሌቦች፣ ዘራፊዎች፣ ቀማኞችና ነጣቂዎች ሞልተው ተርፈዋል፡፡ ሌብነት ቀለምና ዘር የለውም፡፡ ሌባ ሌባ ነው፡፡ ሌባም አሉ፡፡
ምሕረት፣ ሀፍረት፣ ይሉኝታን የማያውቁና አይናቸውን በጨው ያጠቡ ደረቅ ዘራፊዎች ገና መቼ ተጋልጠው ወጡና ነው አሉ ሁሉም በአንድነት፡፡ ሌቦ ሌቦ ነይ የሚለው ዘፈን ቢኖር ውይይታቸው የበለጠ ይደምቅ ነበር፡፡
እነ ሌቦ የራሳቸውን ሰዎች ሲተክሉና ቤት የነበረውን ቤት አልባ ሲያደርጉ፤ ምን ያልተሰራ ስራ አለ፤ የአዲስ አበባ ሹሞች ከቀበሌ ክፍለ ከተማ ምን ያልሰሩት ግፍ አለ ብለሽ ነው አሉ ደቻሳ፡፡ ይሄ ሁሉ ግፍ ሞልቶ ቢፈስ ይኸው ከየት መጣ ሳይባል ድንገተኛ አውሎ ነፋስ እንደ መብረቅ ወርዶ ጉድ አደረጋቸው፡፡ እግዜአብሔር መኖሩን ብቻ ሳይሆን ኃያል መሆኑንም አሳየ አሉ ይመናሹም፡፡ በድንቅ ስራው በመደመም፡፡ ያፈራርሰዋል የሞቀውን ቤት ይሉት አባባል ሆኖ ቢያዩት፡፡ እንዲህ እሳተ ገሞራ አስነስቶ የሚለበልባቸው እግዜሩ እኮ ነው፤ በሰው አድሮ ሌላ እኮ አይደለም አሉ ደቻሳ ደገሙና፡፡
ግፍ እየሰሩ ቤተክርስቲያን ቢሄዱ፤ ምጽዋት ቢሰጡ፤ ቢዘክሩ ከልብ ካልሆነ ምን ያደርጋል አሉ ይመናሹ፡፡ ይውጋህ ይማርህ አይነት መሆኑ ነው፡፡ ገና ብዙ ወደፊት የሚዘረዘሩ የሚፈለጉ ሰዎች መኖራቸውን አትጠራጠሩ፡፡ ይሄ ሁሉ ሲደረግ ሕግና ስርዓት መጥፋቱን፤ ጠያቂ ለምን ባይ አለመኖሩን፤ መካሪ ማጣታቸውን፤ በእብሪት አብጠው ተወጥረው ባሉበት ዙሪያ ገባውን በንዴት የታጀበው የሕዝቡ ቁጣ ብስጭት ንዴት ገንፍሎ ሲወጣ ማንም ሊመክተው አልቻለም እኮ፡፡ ውይይቱ ቀጠለ፡፡ ጨሰ፡፡
በአባት እናት፣ በትልቅ በትንሽ ልጆች፣ እህቶች፣ ወንድሞች፣ የቅርብና የሩቅም ቢሆን ዘመዳ ዘመዱን በየስማቸው የባንክ ደብተር እየከፈቱ ያለፉበትንና ያልደከሙበትን ሀብት እንዲያከማቹ ማድረግ ለሰሚው ለአድማጩ ግራ ነው፡፡ የእነሌቦ ስራ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ታይቶና ተሰምቶ የማይታወቅ የወደፊቱም ትውልድ ከዚህ አይነቱ ነውረኛ ድርጊት እንዲጠነቀቅ ለማስተማሪያነት እንደሚያገለግል መምህር አበበ ግሩም እምግሩማን በሚል ገለጹ፡፡
ለሕጻን ልጅ በስሙ ባንክ አካውንት ተከፍቶ የሚሊዮኖች ገንዘብ ባለቤት ሆኖ እና አንድ ሰው 53 ቤቶች በስሙ በባለቤትነት ተመዝግቦ መገኘቱን በመስማታቸው ጉድ ጉድ ብለው ሊያበቁ አልቻሉም፡፡ ጆሮ አይሰማው የለ መቼም፤ ሰምተንም ሆነ ገምተን የማናውቀው ገና ብዙ ጉድ እንሰማለን አሉ አባባ ደቻሳና ጎረቤቶቹ በመስማማት፡፡
ሥጋ ነጋዴው ወርኬቦ ነገሩ ብዙም ያስደነቀው አልመሰለም፡፡ እናንተ ሰዎች አሁን ሰዎች ለምን ገንዘብ አገኙ ብላችሁ ነው እንዲህ የምትንጫጩት ሲል ጠየቀ፡፡ መለስ አደረገና እሺ ንገሩን ማነው ገንዘብ የሚጠላው አባባ ደቻሳ? እማማ ይመናሹ? እኛ? አላገኘንም ብላችሁ ነው፤ ሰው የሚለፋው የሚደክመው ሀብት ንብረት ለማግኘት አይደለም እንዴ? ብሎ ሲናገር ሁሉም ፍንድቅ… ፍንድቅ.. ብለው ሳቁ፡፡ አባ ግድየለሽ አንተ ምን አለብህ፤ ሥጋህን በላህ፤ ጠጅህን ጠጣህ፤ ሞቅ ብለህ ገባህ፤ ተኛህ፡፡ ነገም እንደዚሁ ነህ፡፡ ወርኬቦ ሰርቶ መክበርና ዘርፎ መክበር አንድ አይደለም አሉት፡፡ ይህ ሁሉ ሀብት ሀገርና ሕዝብ በመዝረፍ የተገኘ በመሆኑ ነው ሕዝቡ የተቆጣው ሲሉት ወርኬቦ ትንሽ የተረጋጋ መሰለ፡፡ ቀጠለና እኔ ምን አገባኝ፤ እኔም ባገኝ አለቅም ሲላቸው ዳግም በሳቅ ተንከተከቱ፡፡ እኔ ወርኬቦ አንድ የራሴን ሥጋ ቤት እንኳን ብከፍት ዲታ እሆን ነበር አለ ድህነቱ እየቆጨው፡፡ ዶሮ ብታልም ጥሬዋን አሉት፡፡ ታዲያ ሌላ ምን ታልም አላቸው በምላሹ፡፡
እንዲህ የሙጭልፍቶች ሀገር ሆና ትቅር አሉ እማማ ይመናሹ በንዴት ጦፈው፡፡ የምንሰማው ሁሉ በእድሜያችን ሙሉ ሰምተን የማናውቀው ጉድ ነው፡፡ ሕዝብን ማስተዳደር እንዴት ሀገርን መዝረፍ ሊሆን ይችላል? በማለት አጥብቀው ይደመማሉ፡፡ ከድሀው መቀነት ፈተውና አሰግደደው የሚወስዱ አይን አውጣ ሌቦች፡፡ እነ ሌቦ ሌቦ ነይ፡፡
በቀበሌ ሌቦች፤ ክፍለ ከተማ ሌቦች፤ በየቢሮው ሌቦች፤ የሰው መሬት ወስደው ካርታ አውጥተው የሚሰጡ ሌቦች፤ ካርታ ሰጪዎቹ ሌቦች፤ ሕዝብን ለማገልገል መንግሥት የመደባቸው መሆኑን ረስተው ሕዝብን የሚዘርፉ የሚያስገድዱ፤ መብቱን ለመጠየቅ ሲሄድ ይሄን ያህል ሺህ ካላመጣህ የጠየከውን አታገኝም ብለው ተደራጅተው ከትንሹ እስከ ትልቁ ድሀውን ጭምር ግጠው የበሉ ያስለቀሱ ሌቦች፤ በድሀው እንባ የሚደሰቱ እርጉማን ፤ ተወው እባክህ ምን ያመጣል? የትስ ቢሄድ የት ይደርሳል? እያሉ ሲሳለቁ የነበሩ ሹምና ምንዝሮች፤ በሕዝብ ላይ የሚፈጸመው ግፍና በደል በዝቶ ጽዋው ሞልቶ ሲፈስ ይኸው ጎርፍ ሆኖ ጠራረጋቸው ሌባ ሁላ አሉ አባባ ደቻሳ፡፡
በቀደም ስለሌቦቹ ብዙ ከሰሙ በኋላ እማማ ይመናሹ አባባ ደቻሳ ጎረቤቱም ሰፈሩም መንደሩም በሙሉ ክፉኛ ተበሳጭተዋል፡፡ ድሮ እኮ እከሌ የመንግሥት ብር ሰረቀ አጭበረበረ ከተባለ ሀገር ምድሩ ያን ሰው ለማየት ይጠየፈው ነበር፡፡ ያውም እኮ አንድ ሺህ ብር የማይሞላ ብር ካጎደለ፤ ከሰረቀ፡፡ ግዜ የወለዳቸው ሌቦች ደግሞ ድፍን ሀገርን ዘረፉ፡፡ እድሜ ደጉ ብዙ አሳየን አሉ ደቻሳ፡፡
ሌብነት ዘር ቀለም ጎሳ የለውም፡፡ ሌቦች በሁሉም ዘር ውስጥ አሉ፡፡ 82 ብሔረሰብ አንቆጥርም፡፡ የሁሉም ሌባ ሌባ ነው፡፡ ግለሰቦች ናቸው በስግብግብነት ዘረፋ ውስጥ የሚገቡት፡፡ ሕዝብ አይደለም፡፡ ሌቦች ራሳቸውን እንጂ ብሔራቸውን አይወክሉም፡፡ ሌቦች በሕግ የሚጠየቁት በግለሰብ ነታቸው ነው፡፡ ከአማራው፣ ከኦሮሞው፣ ከትግሬው፣ ከሶማሌው፣ ከወላይታው፣ ከጋምቤላው…ወዘተ ስለተወለዱ አይደለም፡፡ ለሌባ ጥብቅና የሚቆም ሕዝብ የለም፡፡ ሌባ ሁላ! ሌቦች የዘመን መርገምቶች እንዴት ተደርጎ የማይሆነውን አሉ ደቻሳ፡፡ ደጉን ዘመን ለሀገርና ለሕዝብ ታምነው የኖሩ፤ ተከብረው ያለፉ ታላላቅ ሰዎች በማስታወስ፡፡ ኧረ መስረቅ ነውር ነው፡፡ ሀገርን መስረቅ ሕዝብን መስረቅ የነውርም ነውር የወንጀልም ወንጀል ነው ደገሙት ደቻሳ፤ ሌባ ሁላ ሌቦች ሲሉ፡፡
የእነ ሌቦ ነገር