“ኢትዮጵያ የምትታወቅበት ብዝኃነት በመልካ ኢሬቻ ላይ ይታያል” -ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፡- ኢትዮጵያ የምትታወቅበት ብዝኃነት በመልካ ኢሬቻ ላይ ይታያል፤ ይህ ደግሞ የሀገራችን ሕዝቦች እርስ በእርስ ያላቸውን መቀባበል እና መከባበር እንዲሁም መልካም ምኞት ለዓለም ማኅበረሰብ የሚያሳይ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የ2017 የኢሬቻ በዓልን አስመልክተው ባስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት፤ “ለምለም ሣር ክብርን ፣ ፍቅርን እና መልካም ምኞትን ይወክላል፡፡ ብራ ሽግግር ነው፤ ያለፈውን ወደኋላ ትተን ወደ አዲስ ተስፋ በንጹሕ ኅሊና እንሻገራለን፡፡ ከሕዝቡ እሴት ውስጥ ጎልቶ የሚታየውም ይህ ነው፡፡ ኢሬቻ አንድነት ነው፡፡ ኢሬቻ ኅብረት ነው፡፡

ከኢሬቻው መልካ የሚቀርም ሆነ ወደ ኋላ የሚል የለም፡፡ አባቶችና እናቶቻችን አቆይተው ያወረሱን እሴት ማዳላት የለውም፡፡ ሰው ሁሉ እኩል ነው” በማለት፤ ኢትዮጵያ የምትታወቅበት ብዝኃነት በመልካ ኢሬቻ ላይ እንደሚታይ፤ ይህ ደግሞ የኢትዮጵያ ሕዝቦች እርስ በእርስ ያላቸውን መቀባበል እና መከባበር እንዲሁም መልካም ምኞት ለዓለም ማኅበረሰብ የሚያሳይ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

“ኦሮሞ ሰብአዊነት ከሰው ውጪ ትርጉም የለውም ብሎ የሚያምነው ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ኦሮሞ እና አብረውት የሚኖሩ ሌሎች ሕዝቦችም ፈጣሪ ባበጀው መልካና ወንዝ ላይ እንደሚሰበሰቡ ጠቅሰዋል፡፡ ይህ ደግሞ ወንድማማችነት መሆኑንና ኢትዮጵያ የምትታወቅበት ብዝኃነት በመልካ ኢሬቻ ላይ እንደሚታይ አስታውቀዋል፡፡ “ይህ ደግሞ የሀገራችን

ሕዝቦች እርስ በእርስ ያላቸውን መቀባበል እና መከባበር እንዲሁም መልካም ምኞት ለዓለም ማኅበረሰብ የሚያሳይ ነው” በማለት፤ ወንድማማችነት በቃል ብቻ ሳይሆን በተግባርም እንደሆነ አመላክተዋል፡፡

“ከሌላ የወሰድነው ሳይሆን የተወለድንበት ነው። ከልጅነት እስከ ዕውቀት ያደግንበትና የኖርንበት ነው። ከውጭ እንደሚያዩን ሳይሆን በውስጣችን ከብረት የጠነከረ አንድነት አለ። አንድ ላይ ከቆምን፣ የእኛን መፍረስ ሲያሟርቱ የሚውሉትን ማሳፈር እናውቅበታለን” ብለዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዳሉት፤ ኢሬቻ ዕርቅ ነው፤ ፈጣሪ ደግሞ ዕርቅ ይወዳል። የተጣሉ ሰዎች ቂም ይዘው ለኢሬቻ ወደ መልካ አብረው አይወርዱም። ኢሬቻ መትረፍረፍ ነው፡፡ ኢሬቻ ምስጋና ነው፡፡ ኢሬቻ ልምላሜ ነው፡፡ ለምለም ሣር ክብርን ፣ ፍቅርን እና መልካም ምኞትን ይወክላል። ብራ ሽግግር ነው፡፡

“ያለፈውን ወደኋላ ትተን ወደ አዲስ ተስፋ በንጹሕ ኅሊና እንሻገራለን በማለት፤ ከሕዝቡ እሴት ውስጥ ጎልቶ የሚታየውም ይህ መሆኑን አንስተዋል፡፡

አባቶችና እናቶቻችን አቆይተው ያወረሱን እሴት ማዳላት እንደሌለው ጠቅሰው፤ “ወንድማማችነት በቃል ብቻ ሳይሆን በተግባርም ነው፡፡ ከሌላ የወሰድነው ሳይሆን የተወለድንበት ነው። ከልጅነት እስከ ዕውቀት ያደግንበትና የኖርንበት ነው። ከውጭ እንደሚያዩን ሳይሆን በውስጣችን ከብረት የጠነከረ አንድነት አለ። አንድ ላይ ከቆምን፣ የእኛን መፍረስ ሲያሟርቱ የሚውሉትን ማሳፈር እናውቅበታለን” ሲሉ ገልጸዋል፡፡

“እኛ የኢትዮጵያ ሕዝቦች ፋይዳ በሌላቸውና ማንም ተነሥቶ የግሉን እና የቡድን ፍላጎቱን ለማሳካት የሚያቀብለን አጀንዳ ላይ ጉልበታችንን ከመጨረስ ወጥተን፣ በዋናው ጎዳናችን ላይ እናተኩር፤ ክብርንና ፍቅርን ይዘን ድህነትና ችግር አውልቀን እንጣል። ወደ ብልጽግና መልካ እንገሥግሥ” ሲሉም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

“ያመለጠ ዕድል ድጋሚ አይገኝም። ለዚህ ትውልድ ያለን ዕድል አሁን ነው። በተገኘው ዕድል የሀገራችንን መጪ ጊዜ አሁኑኑ ማበጀት አለብን። እንደ አባቶቻችን ትልቅ የማስተዋል ጉልበት ያስፈልገናል። የወደቀ ሃሳብ ይዘን መደነቃቀፍ ለውድቀት ካልሆነ ወደፊት የምንወነጨፍበት ጉልበት አይሆነንም” ሲሉም መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

አዲሱ ገረመው

አዲስ ዘመን መስከረም 25/2017 ዓ.ም

Recommended For You