የፋሽን ኢንዱስትሪው በቢሊዮን ብር የሚንቀሳቀስበት ትልቅ ቢዝነስ እንደሆነ ብዙዎች ይስማማሉ፡፡ የፋሽን ኢንዱስትሪው ለበርካቶች የሥራ ዕድል የሚፈጥር በመሆኑ ብዙዎች ሕይወታቸውን የሚመሩበት ዘርፍ ነው፡፡ ለዘርፉ የተለየ ትኩረት የሚሰጡ እና ፍላጎት ያላቸው በርካቶችም ሥራቸውን ከሀገራቸው አልፈው በዓለም ደረጃ ለማስተዋወቅ ይጠቀሙታል፡፡ እንደ ግለሰብ ደግሞ ብዙዎች የእለት ስሜታቸውን የሚገልጹበት ነው፡፡ ታዲያ በዚህ ዘርፍ ላይ በአለባበስ፣ በመዋቢያ ምርቶች፣ በተለያዩ ማጌጫዎች ላይ በማምረት ፣ ወደሌሎች ሀገራት በመላክ አልያም ደግሞ እነዚህን ምርቶች በመጠቀም ስማቸው የሚነሱ ሀገራት አሉ፡፡ የፋሽን ኢንዱስትሪው ውስጥ ከሚካተቱ ዘርፎች የውበት ሳሎን ውስጥ የሚሰጡ አገልግሎቶች ተጠቃሽ ሲሆኑ ከእነዚህ ውስጥ እንስቶች በተለያዩ ምክንያቶች ለመረጡት ፕሮግራም እና ቀን የሚጠቀሟቸው ሰው ሰራሽ ጸጉር ዊግ ፣ ሂውማን ሄር የምንለው ይገኝበታል፡፡ እነዚህ የመዋቢያ ምርቶች ወደ ሀገራችን በብዛት ከውጭ የሚገቡ እና ጥቅም ላይ የሚውሉ ናቸው፡፡ በዛሬው የፋሽን ገጻችን እነዚህን ሰው ሰራሽ ጸጉር የተወሰነውን ከውጭ ሀገር በማስገባት ወደተለያየ ዓይነት የሰው ሰራሽ ጸጉር በመቀየር ወደ ገበያ የምታቀርብ አምራች የውበት ሳሎን ባለሙያ ጋር ቆይታ አድርገናል፡፡
ብርዛፍ ኪሮስ ትባላለች በአንድ ወቅት በወሰደችው የውበት ሳሎን ስልጠና አማካኝነት የራሷን የውበት ሳሎን ከፍታ ለሁለት ዓመት ያክል የተለያዩ አገልግሎቶችን ስትሰጥ ቆይታለች፡፡ ‹‹በውበት ሳሎን ውስጥ ስሰራ እነዚህን አርቴፊሻል ጸጉሮች ከገበያ እየገዛሁ ነበር ለደንበኞቼ በማቅረብ እንደሚፈልጉት አድርጌ እሰራቸዋለሁ ፡፡›› የምትለው ብርዛፍ በሂደት በውበት ሳሎኗ ውስጥ በራሷ ለመሥራት ሙከራዎችን አድርጋለች፡፡ በሳሎን ውስጥ እንስቶች የሚጠቀሟቸው ሰው ሰራሽ ጸጉሮች በቁመታቸው መርዘም፣ ባላቸው ጸጉር ብዛት፣ የጸጉሩ አሰራር ዓይነት እንዲመርጧቸው ያደርጋል፡፡ ታዲያ እነዚህ ሰው ሰራሽ ጸጉሮች የተለያየ ዓይነት ሲሆኑ ፍሪዝ ፣ ስትሬት ፣ ዌቭ ሲሆኑ የእንስቷ ጸጉር ላይ በተለያየ መንገድ የሚቀጠሉ ፤ ኮፍያ ተብለው የተዘጋጁ እና እንስቶች በጸጉራቸው ላይ በማጥለቅ ብቻ እስከፈለጉበት ጊዜ ሊጠቀሙባቸው የሚችሏቸው ናቸው፡፡ እነዚህ ሰው ሰራሽ ጸጉሮች ታዲያ በትክክል ለሰው ጸጉር የሚዘጋጁ እና ሴንቴቲክ ተብለው እንዲሁ ከተለያዩ ግብዓቶች ተዘጋጅተው ወደ ሀገራችን ሲገቡ ምርቱን የሚፈልጉ የውበት ሳሎኖችም ሆኑ ግለሰቦች ቀላል በማይባል ዋጋ ይገዙታል፡፡
ታዲያ ብርዛፍ ይህንን ሥራ ቁጥጥር ለመሥራት የሚያገለግለው እና በተለምዶው ዊግ ብለን የምንጠራውን ሰው ሰራሽ ጸጉር ወደ ተለያየ ዓይነት ከላይ ወደ ጠቀስናቸው የጸጉር ዓይነቶች እዚሁ በሀገር ውስጥ መቀየር እንደሚቻል ባረጋገጠች ጊዜ የውበት ሳሎን ውስጥ ጸጉር ከመሥራት እነዚህን ሰው ሰራሽ ጸጉሮች ጥቂት ግብዓቶች ተጠቅማ ወደማምረት ገብታለች፡፡ ስያሜው ‹‹ጎልድ የአርቴፊሻል ጸጉር ማምረቻ›› ሲሆን ሥራውን ስትጀምረው በስሯ ሶስት ሠራተኞች ነበሯት። ‹‹መጀመሪያ ስጀምረው ብዙም ባይሆን አንዳንድ የሚሰሩ ሰዎች ነበሩ ግን እንደዚህ አልተስፋፋም ነበር።›› የምትለው ብርዛፍ ሥራዋ በቀጣይ እንደሚያድግ ታይቷት ነበርና ሥራዋን ማስተዋወቅና ማሳደግ ቀጥላለች፡፡
እነዚህን ሰው ሰራሽ ጸጉር በተለያየ መንገድ ለመሥራት ከኬንያ የሚመጣው እና ለቁጥርጥርና ለሹሩባ የጸጉር አሰራር የሚያገለግለውን እንደ ዋና ግብዓት ትጠቀማለች ፤ ከዚያም ወደሌሎች የጸጉር ዓይነቶች ትቀይራቸዋለች፡፡ ለአብነት ሰዎች ጸጉራቸው የረዘመ የበዛ ሆኖ ለሚፈለጉት ፕሮግራም የስፌት ዊግ ተብሎ የሚዘጋጀውን ጸጉር ለመሥራት የመረጠች እንስት የራሷን ጸጉር ሹሩባ ከተሰራች በኋላ የምትፈልገውን የብዛት መጠን ያለውን ስፌት ዊግ በሹሩባው ላይ ክርን በመጠቀም ከጸጉሯ ጋር እንዲያያዝ ይደረጋል ፤ ነገር ግን ይህ ሂደት እንደ ጸጉሩ የባለሙያዋ ፍጥነት በውበት ሳሎን ውስጥ ከሶስት ሰዓት በላይ ሊወስድባት ይችላል፡፡
ብርዛፍ ይህንን ሂደት ለማስቀረት አንዲት እንስት በምትፈልገው መንገድ ተፈጥሯዊ ጸጉሯን ካስያዘች በኋላ ይህንን በተለያየ መንገድ የተዘጋጀ ጸጉር በጸጉር ማስያዣ ጌጥ ላይ አያይዛ በመሥራቷ በማንኛውም ሰዓት ማድረግ እና ማውለቅ በሌላ ጊዜም ደግማ ለመጠቀም ያስችላታል፡፡ ብርዛፍ በማምረቻ ቦታዋ ከዚህም በተጨማሪ በሀገራችን የተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ የጸጉር አሰራሮች ነገር ግን ሰዎች የተለየ ፕሮግራም ሲኖራቸው የሚያዘወትሯቸውን አልባሶ የሹሩባ ዓይነት በሰው ሰራሽ በኮፍያ መልኩ አዘጋጅታ ለገበያ ታቀርባለች፡፡ ይህም እንስቶች በውበት ሳሎን የሚያጠፉትን ጊዜ በእጅጉ የሚቀንስ ሲሆን በሚሰሩበት ጊዜ የሚኖረውን ህመም ይቀንሳል በሌላ ጊዜም ደግመው መጠቀም የሚችሉት ይሆናል፡፡
ሰው ሰራሽ ጸጉር በሀገር ውስጥ ማዘጋጀት ያልተለመደ በመሆኑ ያለውን ተቀባይነት ብርዛፍ እንዲህ ትገልጻለች ‹‹ ሰዎች ጋር ያለው አቀባበል ጥሩ ነው ለጸጉር ቤቶች ፣ ተረክበው ለሚሸጡ ነጋዴዎች ፣ ወደ ክፍለ ሀገር ለሚወስዱ እና ማምረቻ ቦታችን ላይ መጥተው አንድ ፍሬ ለሚገዙትም ጭምር እናቀርባለን፡፡›› በማለት ትገልጻለች፡፡ በአሁን ሰዓት በስሯ 15 ሠራተኞች ሲገኙ ሴንቴቲክ ተብሎ የሚጠራውን ዊግ ትጠቀማለች ሒውማን ሔር ያረጀባቸው ሰዎች ደግሞ ወደ እሷ በመምጣት እንዲታደስላቸው እና ወደፈልጉት የጸጉር ዓይነት እንዲቀየር ያደርጋሉ፡፡ ሥራውን ለመሥራት የመስፊያ ማሽኖች፣ መጠቅለያዎች ከሀገር ውስጥም ከውጭ የሚመጡ የተለያዩ ጨርቆች እና የውበት ሳሎን መሳሪያዎችን ትጠቀማለች፡፡ ‹‹ሠራተኞችን በአብዛኛው አሰልጥነን ነው የምንቀጥረው በመሆኑም ብዙ ሥራ የሌላቸው ገቢያቸው ዝቅተኛ የሆኑ ሴቶች መጥተው የሥራ እድል ስለሚያገኙ ደስ ይለኛል፡፡›› የምትለው ብርዛፍ፤ ወደፊት ሥራውን በማስፋት ለብዙዎች የሥራ እድል በመፍጠር አሁን ከምታመርተው በበለጠ ጥራትና መጠን ለማምረት ራሷን በሥልጠናዎች የማሳደግ እቅድ አላት፡፡
ሆኑ ወይም ክፉ ናቸው ተብሎ አይጠሉም፤ ሲጀመር ክፋታቸው ለሌላ ሰው እንጂ ለራሳችን አይታየንም። አንዲት ትልቅ ባለሀብት ሴትዮ እና የዕለት ጉርስ የሚቸግራት እናታችንን አናነፃፅርም፡፡ ሀገርም ልክ እንደዚያ መሆን አለበት፡፡ እልህ የምንጋባበት፣ የምናኮርፍበት፣ ቂም የምንይዝበት መሆን የለበትም፡፡ ብዙ ሰዎች ሀገራቸውን ይሳደባሉ፡፡ የተከሰተው ችግር እኮ አብረን የምንፈታው፣ እኛም የመፍትሔው አካል የምንሆንበት እንጂ በእርግማን እና በስደት የምንፈታው አይደለም፡፡
የሰለጠነ ሀገር መኖር ብዙ ውጫዊ ምቾት አለው፤ ችግሩ ግን የህሊና ምቾት የለውም፡፡ እንደ ባሪያ መታየት፣ ነጭ ቆሞ አንተ አትቀመጥም መባል፣ ትሸታላችሁ እየተባለ መገለል… የመሳሰሉት የአዕምሮ ቀውስ ውስጥ ይከታሉ፡፡ በሰው ሀገር የለፋነውን፣ የታገልነውን እና የታገስነውን ያህል በሀገራችን ብንለፋ እና ብንታገስ ለቀጣዩ ትውልድ የተስተካከለች ሀገር እንገነባለን፡፡
እንደ ጃፓን ያሉ ሀገራት አሁን የደረሱበት የሥልጣኔ ደረጃ ላይ የደረሱት ብዙ ዋጋ ከፍለው ነው። ብዙ ተሰቃይተው ነው፡፡ የተማረ ዜጋ አውሮፓ ሄዶ ትምህርት ቀስሞ በሀገሩ ማገልገል እንዳለበት አስገዳጅ ሕግ አውጥተው ነው፤ በሕግ አስገዳጅነት ብቻ ሳይሆን በውስጣቸው አምነው፣ ህሊናቸው ገዝቷቸው፣ ሀገራችንን መለወጥ አለብን ብለው እንደ ዜጋ ቆርጠው ተነስተው ነው፡፡ ስለዚህ በትንሽ ትልቁ ሀገርን እየተሳደቡ እና እየተራገሙ የራስን ሀገር ‹‹ይቺን ሀገር መገላገል ነው!›› ማለት ለሚቀጥሉት ዘመናትም ድሃ እና ኋላቀር ሆና እንድትኖር መፍረድ ነው፡፡
በመንግሥት በኩል ያለውን ችግር ደግሞ እንታዘብ። ዜጎች ተወልደው ያደጉበትን ሀገር ለቀው ለስደት የሚዳረጉት በስደት ውስጥ የሚያጋጥሙ ችግሮችን የማያውቋቸው ሆነው አይደለም፡፡ ሂደቱ ሁሉ አልጋ በአልጋ ይሆናል ብለው አይደለም፡፡ ሀገራቸው ውስጥ የሚያጋጥማቸውን ችግር ‹‹ስደቱ ከዚህ አይከፋም!›› ብለው ነው፡፡ አሁንም ጦርነት ላይ ነን፡፡ አሁንም እልህ መጋባትና ብሽሽቅ ውስጥ ነን፡፡ የኑሮ ውድነት አደገኛ ሁኔታ ላይ ደርሷል፡፡ በተለይም በደሞዝ የሚኖሩ የተማሩ የሚባሉት የህብረተሰብ ክፍሎች ተገቢውን ክብር እያገኙ አይደለም፡፡ በህክምና፣ በመምህርነት፣ በጋዜጠኝነት… በተለያየ ሙያ ላይ ያሉ አዋቂዎች የሰለጠነ ሀገር ውስጥ ‹‹የበግ እረኛ ብሆን ይሻለኛል!›› እያሉ ነው፡፡ በሀገራቸው ውስጥ የሚያገኙት ክብርም ሆነ ጥቅም ከበግ እረኝነት የተሻለ ስላልሆነ ማለት ነው። በዚህ ሁኔታ ከቀጠለ ሀገሪቱ የተማረ ሰው አልባ ትሆናለች ማለት ነው፡፡
እንግዲህ መንግሥት ኢትዮጵያን ለማሰልጠን፣ ኢትዮጵያን ለማበልጸግ፣ ኢትዮጵያን ወደ ከፍታ መውሰድ ከፈለገ… ለቀጣይ ትውልድ መሠረት የሚሆን ነገር ማድረግ አለበት፡፡ ለቀጣዩ ትውልድ የተደራጀች ሀገር ማስረከብ የሚቻለው ደግሞ የተማሩ፣ የነቁ እና የበቁ ሰዎችን በማፍራት እንጂ በማጣት አይደለም፡፡ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ እየተባባሰ የመጣው የታዋቂና አዋቂ ሰዎች ከሀገር መውጣት የሚያስከትለው ችግር ይኖረዋል፡፡
በፖለቲካ ዓይን ካየነውም ‹‹ከሀገር ከወጡ ግልግል!›› የሚባል አይደለም፡፡ በቅሬታ እና በኩርፊያ ከሀገሩ የወጣ ዜጋ ከውጭም ሆኖ ቢሆን አያርፍም፤ ዲፕሎማሲው ላይ የሚፈጥረው ተፅዕኖ ይኖራል።፡ ስለዚህ በፖለቲካው በኩል ያለው ውጥረት መርገብ አለበት፡፡
ይህ ትውልድ አርቆ ማስተዋል መቻል አለበት። አለበለዚያ ተወቃሽ ትውልድ እንዳይሆን ያስፈራል። የሀገር ፍቅር ማለት ምን ማለት እንደሆነ ሊገባን ይገባል፤ አለበለዚያ የተማሩ ሰዎች ስደት በዚሁ ከቀጠለ መበልጸግ አንችልምና ዕጣ ፋንታችን ስደት ብቻ ይሆናል!
ሰሚራ በርሀ
አዲስ ዘመን ሰኞ መስከረም 13 ቀን 2017 ዓ.ም