![](https://press.et/wp-content/uploads/2019/07/11-36.jpg)
የፊንጢጣ ኪንታሮት ወይም ሄሞሮይድ የሚከሰተው በፊንጢጣ ውስጥ የሚገኙ የደም መልስ የደም ስሮች በደም ተወጥረው ሲያብጡ ነው።
የህመሙ ዋና ዋና ምልክቶች
- የኪንታሮት ህመም ምልክቶች እንደኪንታሮቱ ቦታ የሚወሰን ሲሆን የውስጠኛው የኪንታሮት ዓይነት ብዙውን ጊዜ በዓይን የማይታይ ቢሆንም በሚፀዳዱበት ወቅት ማማጥ ካለዎ የደም ስሮቹ ሊቆጡና በቀላሉ ሊደሙ ይችላሉ። አንዳንዴ በሚያምጡበት ወቅት የውስጠኛው ኪንታሮት ዓይነት ወደታች በመምጣትና በፊንጥጣ ውስጥ በማለፍ ህመምና የመቆጥቆጥ ስሜት ሊኖረው ይችላል።
- የውጪኛው የኪንታሮት ዓይነት በፊንጥጣ ዙሪያ ባለው ቆዳ ስር የሚገኝ ሲሆን የደም ስሮቹ በሚቆጡበት ወቅት ሊያሳክኩ ወይም ሊደሙ ይችላሉ። አንዳንዴ ደም በውጭኛው ኪንታሮት ውስጥ በመጠራቀምና በመርጋት ከፍተኛ ህመም፣ እብጠትንና መቆጣትን/ መለብለብን ሊያመጣ ይችላል።
- በሚፀዳዱበት ወቅት/ሰገራ በሚወጡበት ወቅት ከፊንጥጣ የሚወጣ ህመም የሌለው ደም/መድማት፡- ይህን ክስተት በመፀደጃ ሳህን ላይ ወይም በሶፍት ላይ ሊያዩ ይችላሉ።
- በፊንጥጣ አካባቢ የማሳከክ ወይም የማቃጠል ስሜት ካለዎ
- በፊንጥጣ አካባቢ ህመም ወይም ምቾት ያለመሰማት ካለዎ
- በፊንጥጣ ዙሪያ እብጠት ካለዎ
- የሰገራ ማምለጥ ካለዎ
እነዚህ ምልክቶች ከኪንታሮት ውጪ የአደገኛ በሽታ (ለምሳሌ የትልቁ አንጀት ካንሠር) ምልክቶች ሊሆኑ ስለሚችሉ ሀኪምዎን ያማክሩ።
እንዴት መከላከል ይቻላል?
ለኪንታሮት የሚያጋልጠው ዋነኛ ምክንያት የሆድ ድርቀት ነው። በትንሹ በሳምንት 3 ወይም 4 ጊዜ ሠገራ የማይወጣ ከሆነ ሠገራ በትልቁ አንጀት ውስጥ ይደርቃል። ለማስወጣት በጣም መገፋት ይፈልጋል ይህም ግፊት ደም ከፊንጢጣ የደም ስሮች ወደ ልብ እንዳይመለስ በማድረግ እዛው እንዲጠራቀም አድርጎ ኪንታሮትን ያመጣል ከነበረም ያባብሳል።
የሆድ ድርቀትን ለማስወገድ ምን ማድረግ ይቻላል?
- ፍራፍሬ እና አትክልቶችን አዘውትሮ መመገብ (ብዙ ፋይበር ስላላቸው)
- የፋይበር ሰፕለመንት ፓውደር ወይንም ኪኒን (20-35 ግራም ፋይበር በቀን) (ከፋርማሲ)
- ሠገራ የሚያለሰልሱ ከፋርማሲ ያለሀኪም ትእዛዝ የሚሸጡ (docusate, psyllium, wheat dextran ወይም methylcellylose) መውሰዱ። ሀገር ውስጥ ላይኖሩ ይችላሉ። በውጭ ሀገር በቀላሉ የሚገኙ ናቸው።
ህመም እና ማሳከኩን ለመቀነስ
- ለብ ያለ ውሃ ሠፋ ባለ ዕቃ ሞልቶ ከ 10- 15 ደቂቃ በመቀመጫ መቀመጥ።
- ምንም ነገር ውሃው ውስጥ መጨመር አያስፈልግም።
- ያለሀኪም ትዕዛዝ የሚሸጡ የኪንታሮት ህመም ማስታገሻዎችን መጠቀም (በሚቀባ ወይንም በፊንጢጣ በሚገባ) ፋርማሲስቱ በሚመክረው መልኩ መጠቀም።
- ሀይድሮኮርቲሶን(hydrocortisone) በውስጣቸው የያዙ መድኃኒቶችን ከ1 ሳምንት በላይ መጠቀም አይመከርም።
- ከላይ የተዘረዘሩት መድኃኒቶች ባያሽሉ
- በቀላል ቀዶ ሕክምና ኪንታሮቶችን ማጥፋት ይቻላል። ለዚህ ሀኪምዎን ያማክሩ።
- አንድ ጊዜ ኪንታሮት ጠፋ ማለት ተመልሶ አይመጣም ማለት አይደለም።
እንዳይመለስ ከላይ የዘረዝርናቸውን ይተግብሩ።
የባህል ህክምና መሄድ ይመከራል?
የባህል ህክምናው የተለያየ ቢሆንም በአብዛኛው ሲደረግ የምንመለከተው ያበጠ የሚመስለውን ቦታ በመሰንጠቅ ወይንም በመውጋት የተለያዩ ቅጠሎችን በመቅበር እንዲቆስልና ተቀርፎ እንዲወድቅ ማድረግ ነው። በእርግጥ የተወሰኑ ሰዎች በዚህ ህክምና የዳኑ መሆኑን ቢናገሩም ብዙ ለስቃይ የተዳረጉ ሰዎች አሉ። በተለይም ህመሙ የሚከሰትበት ስፍራ አብዛኛውን ጊዜ ንፅህናውን ያልጠበቀ ስለሚሆን ቁስሉ ለኢንፌክሽን ይጋለጣል። መግል ይቋጥራል ያመረቅዛል። ይህም ለመዳን ረጅም ጊዜ እንዲፈጅበት ያደርጋል።
ቶሎ ካልታከመ ለሕይወት አደገኛ ሊሆን ይችላል። ሌላው እና ዋነኛው ችግር ደግሞ ቁስሉ ሲድን ጠባሳ ስለሚተው ወደፊት የፊንጢጣ መጥበብ ያመጣና ሠገራ መውጣትን እስከነአካቴው ይከለክላል። ቁጥራቸው ትንሽ የማይባሉ ሰዎች በዚህ ሁኔታ ተሰቃይተው መፍትሄ ፍለጋ ወደ ሀኪም ቤት የሚሄዱ ቢሆንም በርካታ ህሙማንም ባህላዊ ህክምናን ተመራጭ ያደርጋሉ። በእርግጥ የባህል ህክምና ለአንዳንድ በሽታዎች መፍትሄ የሚሠጥ መሆኑን ቢታመንም ለኪንታሮት ህክምና ግን ከጥቅሙ ጉዳቱ ስለሚያመዝን እንዲሄዱ አይመከርም። በመሆኑም ምልክቶቹን በማየት ቀድሞ ሐኪምን ማማከር ተገቢ መሆኑን ነው ባለሙያዎች የሚያስገነዝቡት።
ምንጭ፡– ጤነኛ ድረ ገፅ
አዲስ ዘመን ቅዳሜ ሰኔ 29/2011
Your place is valueble for me. Thanks!…
Your place is valueble for me. Thanks!…
Hello would you mind letting me know which webhost you’re working with? I’ve loaded your blog in 3 completely different web browsers and I must say this blog loads a lot faster then most. Can you recommend a good web hosting provider at a honest price? Thanks, I appreciate it!
This blog is definitely rather handy since I’m at the moment creating an internet floral website – although I am only starting out therefore it’s really fairly small, nothing like this site. Can link to a few of the posts here as they are quite. Thanks much. Zoey Olsen
An impressive share, I just given this onto a colleague who was doing a little analysis on this. And he in fact bought me breakfast because I found it for him.. smile. So let me reword that: Thnx for the treat! But yeah Thnkx for spending the time to discuss this, I feel strongly about it and love reading more on this topic. If possible, as you become expertise, would you mind updating your blog with more details? It is highly helpful for me. Big thumb up for this blog post!
Very well written post. It will be beneficial to everyone who utilizes it, as well as myself. Keep up the good work – can’r wait to read more posts.
Whats up this is kind of of off topic but I was wondering if blogs use WYSIWYG editors or if you have to manually code with HTML. I’m starting a blog soon but have no coding expertise so I wanted to get guidance from someone with experience. Any help would be greatly appreciated!
Would love to incessantly get updated outstanding site! .
Upgrade your style with Marc Jacobs deals at the marc jacobs factory outlet online.
Very well written article. It will be supportive to everyone who employess it, including yours truly :). Keep doing what you are doing – looking forward to more posts.
Hi there very nice web site!! Man .. Excellent .. Amazing .. I’ll bookmark your site and take the feeds also…I’m happy to find so many helpful info here in the post, we want work out extra strategies on this regard, thanks for sharing.
Explore the latest trends in shoes and clothing at ayouba.com.
Hi! This is my first visit to your blog! We are a group of volunteers and starting a new project in a community in the same niche. Your blog provided us useful information to work on. You have done a outstanding job!
Your style is so unique compared to many other people. Thank you for publishing when you have the opportunity,Guess I will just make this bookmarked.2
Oh my goodness! an amazing article dude. Thank you However I am experiencing subject with ur rss . Don’t know why Unable to subscribe to it. Is there anybody getting identical rss drawback? Anybody who knows kindly respond. Thnkx
This actually answered my downside, thanks!
Hello there, I discovered your web site by means of Google even as searching for a similar matter, your site got here up, it seems to be good. I’ve bookmarked it in my google bookmarks.
Way cool, some valid points! I appreciate you making this article available, the rest of the site is also high quality. Have a fun.
This web site is really a walk-through for all of the info you wanted about this and didn’t know who to ask. Glimpse here, and you’ll definitely discover it.
Spot on with this write-up, I truly suppose this web site wants far more consideration. I’ll most likely be once more to learn much more, thanks for that info.