የኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት መሠረታዊ የዜጎች ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች መከበር እንዳለባቸው ይደነግጋል።ለዜጎች በሰላም ወጥቶ መግባት፣በማንኛውም የሀገሪቱ ክፍል ተዘዋውሮ የመስራትና የመኖር ነፃነት፣የመደራጀትና ሃሳብን በነፃነት የመግለጽ መብቶች ወዘተ…የሚያከብር ነው። ነገር ግን በሕገ መንግሥቱ የተደነገጉ ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች በሚፈለገው መልኩ ባለመተግበራቸው ችግሮች ተፈጥረዋል። እነዚህን ችግሮች ለመፍታት መንግሥት በተለይ ካለፈው ዓመት መጋቢት ወር ወዲህ በርካታ ሥራዎችን ሰርቷል።
መንግሥት ችግሮቹን ለመፍታት በትኩረት ከሠራው ሥራ አንዱ የፖለቲካ ምህዳሩን የማስፋት ነው። የፖለቲካ ምህዳሩን ለማስፋት በተወሰደው እርምጃ እርስ በርስም ሆነ ከመንግሥት ጋር ሲዋጉ የነበሩ ከ10 የሚበልጡ የታጠቁ ኃይሎች ወደ ሀገራቸው ገብተዋል። ከ45 ሺ የሚበልጡ ዜጎች በምሕረት አዋጅ ተጠቃሚ ሆነዋል። ከ100 ሺ በላይ እሥረኞች ከሁሉም ክልሎች ተፈትተዋል።ይህም በማኅበረሰቡ ውስጥ ተፈጥሮ ለነበረው ፖለቲካዊ ጭንቀት እፎይታን ሰጥቷል።
ከ260 በላይ ሚዲያዎችና ድረ ገጾች ከእግድ ተላቅቀው የሐሳብ ገበያውን ተቀላቅለዋል።፡ የውይይትና ክርክር ባሕልን ለማዳበር የሚረዱ የፓርቲዎች፣ የሚዲያዎችና የምሁራን ውይይቶች ታቅዶባቸው በስፋት ተካሂደዋል፤እየተካሄዱም ናቸው።
ባለፈው አንድ ዓመት የተሠሩት የፖለቲካ ሥራዎች ዋነኛ ግብ የሕዝብን የለውጥ ፍላጎት ለማርካት እና ሀገርን ከትርምስና ከመፍረስ አደጋ ለመታደግ፣ ለሕዝብ ምሬት መንስኤ የሆኑ ሕጎችን፣ ተቋማትንና አሠራሮችን ለማሻሻል፤ በእነዚህም ጥረቶች ሀገሪቱን ከአደጋ ጎዳና መመለስና ሰላምን ማስፈን መቻል ነው። በዚህም ሀገሪቱን ከአደጋ መታደግ ተችሏል።
የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ሂደት የነበረበትን የምህዳር ጥበትና ተግዳሮት በማሻሻል ደረጃ በደረጃ ወደ ሠለጠነ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ለመሻገር፣ በሕግ ከመገዛት በሕግ ወደ መተዳደር ለማሸጋገር ጥረት ተደርጓል።
በአንድ በኩል በተከታታይ የተወሰዱት ፈጣንና ሰፊ የለውጥ እርምጃዎች ሕዝብ ከለውጡ የሚጠብቀው ነገር እንዲጨምር አድርገውታል። በሌላ በኩል ደግሞ የተገኙት ድሎች በመብትና በግዴታ መካከል የፈጠሩት ግርታ አለመረጋጋት እንዲፈጠር ምክንያት ቢሆንም ሰላምና መረጋጋት ለማስፈን እንዲሁም የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ እርምጃዎች ተወስደዋል።
የፍትሕ አካላትን ለማሻሻልና ለማጠናከር ከተወሰዱ እርምጃዎች በተጨማሪ በተደራጁ ቡድኖች በመንቀሳቀስ፣ በሰብዓዊ መብት ጥሰትና በከባድ የሙስና ወንጀል የተጠረጠሩ የሥራ ኃላፊዎችና ግብረ-አበሮቻቸው በሕግ ተጠያቂ እንዲሆኑ ተደርጓል። ለአብነትም በሀገራችን ላይ ከፍተኛ የሽብር ተግባር ለመፈጸም ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 48 የሽብር ቡድን አባላትን በቁጥጥር ሥር በማዋል ያሰቡት የሽብር ጥቃት ሳይፈጸም መከላከል ተችሏል። ብሔርን መሠረት ያደረጉ ግጭቶችን በመቀስቀስና ጥቃቶችን በማድረስ እንዲሁም ዜጎችን በማፈናቀል ወንጀሎች ውስጥ የተሳተፉ 799 ተጠርጣሪ አመራሮችና የጸጥታ አካላት ተይዘው ለሕግ ቀርበዋል።
ሰላምን ለመጠበቅ ልዩነትን የመፍቻ ነባር መንገዶችን በመጠቀም ዘላቂ የሰላም ግንባታ ሥራዎችም ተከናውነዋል። የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ እናቶችና ወጣቶች በዚህ ረገድ በርካታ እንቅስቃሴዎችን አድርገዋል።
በዚህም በክልሎች መካከል ተፈጥረው የነበሩ መካረሮች በአንፃሩ መርገብ፣ በእስልምና ሃይማኖት አመራሮች መካከል የነበረው ክፍፍል መፈታትና ሌሎችም በርካታ ስኬቶች ተመዝግበዋል። አሁንም መሻገር ያሉብን በርካታ መሰናክሎች ቢኖሩም በለውጡ ማግስት ከነበርንበት ግርግር ወጥተን ወደ ተሻለ የመስከን ሂደት እየተሸጋገርን እንገኛለን።
እነዚህና ሌሎች ሥራዎች የተሰሩት በሕገ መንግሥቱ የተደነገጉ የዜጎች ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ተግባራዊ ለማድረግ መሆኑ መታወቅ አለበት። ሕገ መንግሥቱ የሀገሪቱ የበላይ ሕግ በመሆኑ የሚደግፉትም ሆነ የሚቃወሙት ሕጉን መሠረት አድርገው በማክበርና በማስከበር መሆን አለበት።
ሕገ መንግሥቱ ባጎናጸፈው መብት እየተጠቀሙ ፀረ ሕገ መንግሥት ተግባራት ማከናወንም ሆነ ሕገ መንግሥቱ መነካት የለበትም የሚሉ ወገኖች ሁለቱም ዋልታ ረገጥ መሆናቸውን አውቀው ለመቀራረብ መስራት ይጠበቅባቸዋል።ሕገ መንግሥቱ የሚሻሻልበት የራሱ አንቀጽ አለው። ለማሻሻልም ፣ ለመቀየርም የሚፈልገው ኃይል በሕገ መንግሥቱ መሠረት መሆን አለበት። ከዚህ ውጪ ያለው አካሄድ ተቀባይነት የለውም።
በሌላ በኩል ከደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል እየተነሱ ያሉ የክልል እንሁን ጥያቄዎች ሕገ መንግሥታዊ ናቸው። ስለሆነም ምላሻቸውም በሕገ መንግሥቱ ብቻ የሚሠጥ ይሆናል።ስለሆነም መብትን ለመጠየቅ ያስቻለንን ሕገ መንግሥት ማክበር ያስፈልጋል። ከዚህ ውጪ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ግን ፀረ ሕገ መንግሥት መሆናቸው መታወቅ አለበት።
ስለሆነም ሕገ መንግሥቱን ማክበርም ማስከበርም ከሁሉም ዜጋ ይጠበቃል። ማንኛውም የፖለቲካ ኃይል ሆነ ኅብረተሰብ መብት ለመጠየቅ የሚጠቅሰውን ሕገ መንግሕት ማክበርና ማስከበር አለበት። ለጥያቄዎች ሁሉ በጊዜ ቅደም ተከተል ሕገ መንግሥታዊ ምላሽ እስኪሰጥም በትእግስት መጠበቅ ይገባል።
አዲስ ዘመን ቅዳሜ ሰኔ 29/2011
Next time I read a blog, Hopefully it won’t disappoint me as much as this one. After all, I know it was my choice to read, however I really thought you would probably have something helpful to say. All I hear is a bunch of whining about something that you could possibly fix if you were not too busy searching for attention.
Hi, I do believe this is an excellent blog. I stumbledupon it 😉 I will come back yet again since I book-marked it. Money and freedom is the greatest way to change, may you be rich and continue to help other people.
Aw, this was a really nice post. Taking the time and actual effort to generate a good article… but what can I say… I put things off a whole lot and don’t manage to get nearly anything done.
Everyone loves it whenever people come together and share thoughts. Great blog, keep it up.