![](https://press.et/wp-content/uploads/2019/07/ታተተተ-2-11-3.png)
ወቅቱ የተማሪዎች መመረቂያ ነው፤ በያዝነው ዓመት ከ44 በማያንሱ ዩኒቨርሲቲዎች ከ100ሺ በላይ ተማሪዎች ይመረቃሉ፡፡ ተማሪዎቹ በመጀመሪያ፣ በሁለተኛና በሶስተኛ ዲግሪ ደረጃ የሚመረቁ ሲሆን፤ አሁን አሁን ተማሪዎች የመመረቂያ ጥናቶች የሚያካሂዱት፤ ለጥናታቸው ማብራሪያ (defiance) የሚቀርቡት ለይስሙላ እንጂ በትክክል ደረጃቸውን አሟልተውና በአግባቡ ሰርተው አለመሆኑ እየተገለፀ ነው፡፡ አንዳንዶች በአግባቡ ሰርተው የሚያቀርቡትም የሚገባቸውን ውጤት እያገኙ አለመሆኑ እየተነገረ ነው፡፡
ውጤቶች የሚሰጡት በሰፈር ልጅነት፣ በአብሮ አደግነት፣ በፆታ ግንኙነትና በትውውቅ መሆኑ ከመናፈሱም በላይ፤ በተለይ በሁለተኛ እና በሶስተኛ ዲግሪ ደረጃ በሚማሩ ተማሪዎች የሚካሄዱ ጥናቶች ውጤት አሰጣጥ ፍትሃዊነት የጎደላቸው መሆናቸው እየተገለፀ ነው፡፡ የውጤት አሰጣጦች ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እጅግ ባልተገባ መልኩ አማካሪውን በትክክል ሳያማክር፤ ፈታኙም የተማሪውን ምርምር በደንብ ሳያይ በቸልተኛነት የሚሰጡ ነጥቦች በተማሪዎች ዘንድ ከፍተኛ ተፅዕኖ በመፍጠር ላይ መሆናቸው እየተነገረ ነው፡፡
የለፋው የልፋቱን ውጤት የማያገኝበት፤ ያልደከመው ምናልባትም የኮረጀው ደግሞ ከፍተኛ ውጤት የሚያገኝበት ሁኔታ እየታየ መሆኑ የአደባባይ ሃቅ ሆኗል፡ ፡ ይህን እውነታ በቅርብ ዓመታት ውስጥ ዩኒቨርሲቲ የገቡ እና ተምረው ያጠናቀቁ በሙሉ ሳይብከነከኑበት አልቀረም፡፡
ጉዳዩ እየተስፋፋ በመምጣቱ እጅግ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል፡፡ ይህ የደከሙትን የሚያሸማቅቅ እና ሞራል የሚነካ ተግባር እየተፈፀመ ያለው በተለያየ መልኩ ሲሆን፤ አንዳንዴ ሆን ተብሎ፤ ሌላ ጊዜ ደግሞ ባለማስተዋል የሚፈፀም ሲሆን፤ በጉዳዩ ላይ ጥናት ቢጠና አገር ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያስከተለ መሆኑ በታወቀ ነበር፡፡
በዩኒቨርሲቲዎች በአማካሪዎች እና በፈታኞች መመሳጠር፤ አማካሪውን በማክበር፤ አማካሪውን በመጥላት፤ አማካሪውን ለመበቀል ሲባል እና በሌሎችም ምክንያቶች ምንም እንኳ ተማሪው ለፍቶ ለአገር ጥቅም ሊያስገኝ የሚችል ጥናት ቢያዘጋጅም ጥናቱን ሳያገላብጡ እና ጊዜ ወስደው ሳያዩ በጭፍን ውጤት በመስጠት የነገውን የተማሪ ተስፋ የሚያጨልሙ አሉ፡፡
በሌላ በኩል ሙሉ ለሙሉ ኮርጀው ከፍተኛ ውጤት የሚያገኙ ያሉ ሲሆን፤ ብዙም ሳይደክሙ ከሚማርበት ደረጃ በታች ጥናት ያቀረቡም ከፍተኛ ውጤት እየተሰጣቸው ነገሮች ሁሉ ተገላቢጦሽ ሆነው እየታዩ ነው፡፡ ይህ በተማሪዎቹ ህይወት ላይ ከሚፈጥረው ተፅዕኖ ባሻገር በአገር ላይ የሚያስከትለው ጉዳትም ከፍተኛ ነው፡፡
ዩኒቨርሲቲዎች የሚያስተምሩላቸውን መምህራኖች የሚመለምሉት በሁለተኛ ዲግሪ የመመረቂያ ፅሁፍ ቢያንስ በጣም ጥሩ እና ከዚያ በላይ ውጤት ማምጣት አለባቸው ይላሉ፡፡ በጣም ጎበዝ ተማሪ በግምገማ ስህተት ከዛ በታች ከተሰጠው ዩኒቨርሲቲ የማስተማር ዕድሉን አያገኝም ማለት ነው፡፡
በተቃራኒ ደግሞ አቅም ሳይኖረው በስምምነትም ሆነ በቸልተኝነት በአጋጣሚ እጅግ በጣም ጥሩ ያገኘው ተማሪ የዩኒቨርሲቲ መምህር ይሆናል፡፡ ብቃት የሌለው መምህር ዩኒቨርሲቲ ሲያስተምር ተፅዕኖው የትምህርት አሰጣጡ ድረስ የሚዘልቅ ይሆናል፡፡ ብቃት በሌለው መምህር የተማረ ሃኪም፣ ኢንጂነር፣ ዶክተርም ሆነ የሌላ ዘርፍ ሰው የተሟላ ባለሙያ መሆን አይችልም፡፡ ይህ አገሪቷ ላይ የሚያደርሰው ኪሳራም በቀላሉ የሚገመት አይሆንም፡፡
በዩኒቨርሲቲዎች የማይገቡ ውጤቶች የሚሰጡት አንዳንዴ በአማካሪዎች እና በፈታኞች ስግብግብነት መሆኑም እየተገለፀ ነው፡፡ የአንድ ሰው አቅም ውስን ቢሆንም ከአራት በላይ ሰው ለማማከር ጊዜውም ሆነ አቅሙ የሚገድብ ሆኖ ሳለ እስከ 20 ተማሪ ለማማከር እንደሚሞከር፤ አንድ ሰው የውስን ሰዎችን ጥናት መርምሮ መፈተን ቢኖርበትም ምንም ዝግጅት ሳያደርግ ጥናቶቹንም ሳያነብ ብዙ ፈተናዎችን እንደሚፈትን ውጤትም ሲሰጥ በመሰለው፤ ተማሪው ላይ እና አገር ላይ የሚፈጥረውን ተፅዕኖ ግምት ውስጥ ሳያስገባ መሆኑ እየተነገረ የሚገኝ በመሆኑ ይህ ጉዳይ ሥርዓት ሊበጅለት ይገባል፡፡
አንድ ሰው ውስን ሰውን እንዲያማክርም ሆነ እንዲፈትን በህግ ከማስቀመጥ ባሻገር ህጉ ተግራዊ እንዲሆን ክትትል ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ በእርግጥ ሁሉም የዩኒቨርሲቲ መምህራን ይህን ባያደርጉም ቁጥራቸው ቀላል የማይባሉ ሰዎች በመስማማት አንዱን የመጥቀም ሌላውን የመጉዳት ተግባራቸውን ሊያቆሙ ይገባል፡፡
አማካሪ ብቻ ሳይሆን ረዳት አማካሪ፤ የውስጥም ሆነ የውጭ ፈታኝ እንዲሁም ተቆጣጣሪ ቢኖርም፤ በስራ ጫና በሚሰሯቸው ስራዎች የሚፈጥሯቸው ስህተቶች ከመኖራቸውም ባሻገር፤ ሃላፊነታቸውን በአግባቡ እየተወጡ ባለመሆኑ ይህን ተግባር የሚፈፅሙ ሁሉ በደንብ ራሳቸውን ማየት አለባቸው፡፡
መንግስት እና የሚመለከታቸው አካላት በሙሉ በጉዳዩ ላይ ግልፅ ውይይት እንዲኖር ከማመቻቸት ባሻገር ጥናት ማስጠናት እና ለጉዳዩ መፍትሄ ማምጣት ካልተቻለና አሁን ያለው ሁኔታ ከቀጠለ ጉዳዩ አስጊ እንደሚሆን አያጠያይቅም፡፡
አዲስ ዘመን ሰኔ 28/2011
Way cool! Some extremely valid points! I appreciate you penning this write-up and the rest of the website is also really good.
A motivating discussion is worth comment. I think that you ought to write more on this topic, it may not be a taboo matter but usually people don’t talk about these issues. To the next! Many thanks.
This site was… how do you say it? Relevant!! Finally I have found something which helped me. Thanks!
This web site certainly has all of the information I wanted concerning this subject and didn’t know who to ask.
I love looking through an article that will make people think. Also, many thanks for allowing for me to comment.
May I just say what a comfort to discover somebody who genuinely understands what they are talking about online. You actually understand how to bring an issue to light and make it important. A lot more people should read this and understand this side of your story. It’s surprising you are not more popular because you definitely possess the gift.
This is the perfect site for anybody who wants to find out about this topic. You realize so much its almost hard to argue with you (not that I personally would want to…HaHa). You certainly put a brand new spin on a subject that has been discussed for years. Great stuff, just excellent.
I wanted to thank you for this excellent read!! I definitely loved every bit of it. I’ve got you book marked to check out new stuff you post…
Spot on with this write-up, I really believe this web site needs a great deal more attention. I’ll probably be returning to see more, thanks for the advice!
This is a very good tip particularly to those fresh to the blogosphere. Brief but very precise information… Thanks for sharing this one. A must read article!
I like it whenever people get together and share ideas. Great blog, stick with it!
You made some really good points there. I looked on the internet to learn more about the issue and found most people will go along with your views on this web site.
There is certainly a lot to know about this issue. I love all of the points you made.