እንደ ዕድል ሆኖ መልካም ነገሮች ሁሉ ያለዋጋ አይገኙም። በሌላ አነጋገር ጠቃሚና ፋይዳቸው የጎሉ ጉዳዮች የጊዜ፣ የገንዘብ፣ የጉልበት የአካልና አንዳንዴም የህይወት ዋጋን ያስከፍላሉ። ለራሳቸው፣ ለቤተሰባቸው እና ለአገራቸው ጥቅምና ለውጥ ሙሉ ጉልበታቸውን፣ ጊዜያቸውንና ህይወታቸውን ጭምር ሰውተው የሚታትሩ እልፍ ግለሰቦች ያሉትን ያህል መልካም ነገር የማይታያቸውና ከለውጥ ይልቅ ነውጥና ጥፋት የተጠናወታቸው ለእኩይ ዓላማቸው ሲሉ ንጹሃንን የሚገድሉ ግለሰቦችም ቁጥር ቀላል አይደለም።
በዓለማችን ላይ ለህዝቦች ህይወት መሻሻል ታላላቅ ፋይዳ ያበረከቱ ግለሰቦች በተደጋጋሚ ጊዜ ህሊናቸው በግድያና በጥፋት በተሞላ ግለሰቦች ተጠቅተዋል፤ ተገድለዋልም። ገዳዮቹ ህሊናቸው ስለታወረና ማመዛዘን ስለተሳናቸው ባይረዱትም ለህዝብ የሚጠቅሙ ግለሰቦችን መግደል አገርና ህዝብን መግደል ነው። ምክንያቱም ከመኖራቸው የሚጠቀም በርካታ አገርና ህዝብ አለና!
በአገራችንም ለህዝቦች ነጻነት፣ ደህንነት፣ ሰላምና ዴሞክራሲ መተኪያ የሌላት ህይወታቸውን፣ የወጣትነት ዕድሜያቸውንና አካላቸውን የገበሩ ሚሊዮን ጀግኖች ነበሩን፤ አሁንም አሉን። ወራሪ ጠላትን ከአገር በመጠራረግ አምባገነናዊ ስርዓትን በእልህ አስጨራሽ ትግል በማስወገድ ለዛሬው ነጻነትና ዴሞክራሲ ያበቁንን ክቡር ሰማዕታት ለዚህ ምሳሌ አድርገን ማቅረብ እንችላለን። እኒህ ክቡር ዜጎቻችን ያን መስዋዕትነት ባይከፍሉልን ኖሮ አሁን እንገኝበት የነበረውን ባርነትና ጭቆና ማሰቡ ከባድ አይሆንም።
ይህ ሁኔታ ዛሬም ቀጥሎ ለህዝብና ለአገር ለውጥ የታገሉና የተጉ ክቡር ኢትዮጵያውያን ህይወት በግፈኞች ሲነጠቁ አስተውለናል። ቅዳሜ ሰኔ 15 ቀን 2011 ዓ.ም በባህር ዳርና በአዲስ አበባ በአማራ ክልልና በመከላከያ ከፍተኛ አመራሮች ላይ ከአዕምሯቸው ይልቅ በዝናር በሚያስቡ ሰይጣናዊ ሃይሎች የተደረገው የግድያ ወንጀል የብዙዎችን ልብ የሰበረና አገርን ማቅ ያለበሰ እኩይ ተግባር ነው።
በሁለቱም ከተሞች የግድያ ወንጀል የተፈጸመባቸው ውድ ሰማዕቶቻችን ይህ አስከፊ ድርጊት የተፈጸመባቸው ቅዳሜ የእረፍት ቀን ነው ብለው ሲዝናኑ ወይም ከቤተሰቦቻቸው ጋር የዕረፍት ጊዜያቸውን ሲያሳልፉ አልነበረም። ይልቁኑ የአገር ሰላምና ለውጥ እንዲሁም የህዝብ ደህንነትና የህይወት ለውጥ አንገብግቧቸው ትርፍ ጊዜያቸውንም ጭምር መስዋዕት አድርገው ሲሰሩ እንጂ! ጤነኛ ህሊና ላለው ሰው ይህ ድርጊት እጅጉን ያሳምማል። ይህን ወንጀል የበለጠ አስከፊ የሚያደርገው ደግሞ በተለይ ዛሬ ዛሬ ማንኛውም ሃሳብ በነጻነት ተሰንዝሮ አሸናፊው ሃሳብ በውይይት በሚለይበት ጊዜ ላይ መፈጸሙ ነው።
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድም “እነዚህ ሰማዕታት እንደ አለት የጸኑ፣ እንደ አልማዝ የጠነከሩ፣ ሀገራቸውን ከምንም ነገር በላይ የማገልገል ዓላማን ያነገቡ፣ ዓላማቸውን ሳያሳኩ አንገታቸውን ላለማዞር የቆረጡ፣ ይህንንም በተግባር ያረጋገጡ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች ነበሩ” ሲሉ ከገለጿቸው በኋላ “ታላቂቱን ሀገር ማሳነስ፣ የከበረውም ሕዝብ ማዋረድ፣ ለግስጋሴያችን ልጓም፣ ለመንገዳችን እንቅፋት ማኖር ሙያ የሚመስላቸው እዚህም እዚያም አሉ፡፡ ከዴሞክራሲ ሕዝብ ያተርፋል፤ እነርሱ ግን ይከስራሉ፤ ከሥልጣኔ ሕዝብ ይጠቀማል፤ እነርሱ ግን ይጎዳሉ፤ በኅብረ ብሔራዊነት ሀገር ይበለጽጋል፤ እነርሱ ግን ይደኸያሉ፤ በፍቅርና በይቅርታ ኢትዮጵያ ትታከማለች፤ እነርሱ ግን ይታመማሉ፡፡ ይህ ነው የጠላቶቻችን ትልቁ መለያቸው” ብለዋል።
እውነት ነው ለአገርና ለህዝብ ዕድሜን ሙሉ ለፍተው መልካም አሻራን አስቀምጠው የሚያልፉ እጅግ ጥቂት ናቸው። እነዚህ ሰማዕታትም ከእነዚህ መካከል ናቸው። ስለሆነም ዕድሜያቸውን ሙሉ ለህዝብ ጥቅም ኖረው፣ ለህዝብ ጥቅም ታግለው፣ ለህዝብ ጥቅም ሲሉ ኢትዮጵያ ሆነዋልና በኢትዮጵያውያን ልብ ለዘላለም ሲዘከሩ ይኖራሉ። ከቀደምት ኢትዮጵያውያን ሰማዕታትና ጀግኖችም ጋር ይደመራሉ።
ቅዱስ መጽሀፍ ከሰው ልጅ ህያው ማነው? ሞትንስ የማያይ ማነው? እንዲል በዚህች ምድር ላይ ለዘላለም የሚኖር ማንም የለም። ትልቁ ጉዳይ ስንኖር ለህዝብና ለአገር የሚጠቅም ስራ ሰርቶና ስምን ከመቃብር በላይ አድርጎ ማለፉ ነው። ከዚህ አንጻር አኩሪ መስዋዕትነትን የከፈሉት ሰማዕታት እስከመጨረሻው ትንፋሻቸው ድረስ አገርና ህዝባቸውን እያገለገሉ ነፍሳቸው በግፍ ተነጥቃለችና ክብርና ሞገስ ይገባቸዋል እንላለን!
አዲስ ዘመን ሰኔ 20/2011
I blog often and I truly appreciate your content. This great article has really peaked my interest. I’m going to take a note of your website and keep checking for new information about once a week. I subscribed to your RSS feed as well.
Your style is very unique compared to other folks I’ve read stuff from. Many thanks for posting when you’ve got the opportunity, Guess I will just bookmark this blog.
Good post. I learn something totally new and challenging on sites I stumbleupon every day. It’s always interesting to read through content from other writers and use a little something from other websites.
Hello there! I could have sworn I’ve been to your blog before but after going through many of the articles I realized it’s new to me. Anyhow, I’m certainly delighted I came across it and I’ll be bookmarking it and checking back regularly.
Pretty! This was an incredibly wonderful post. Thank you for providing this information.
You ought to be a part of a contest for one of the most useful websites on the net. I’m going to highly recommend this web site!
An outstanding share! I have just forwarded this onto a co-worker who was doing a little research on this. And he in fact ordered me lunch due to the fact that I stumbled upon it for him… lol. So let me reword this…. Thanks for the meal!! But yeah, thanks for spending the time to discuss this topic here on your web page.
There’s definately a great deal to know about this issue. I like all of the points you’ve made.