መጥፎ የአፍ ጠረን(ሃሊቶስስ) የአፍን ንፅህና በደንብ ካለመጠበቅ የሚከሰት ችግር ቢሆንም ሌሎች የአፍና የጥርስ ንፅህና ቢጠበቅም ለህክምና አስቸጋሪ የሆኑ መንስኤዎችም አሉት። ይህ ሁኔታ ሲከሰት ከማስጨነቁም በላይ የታማሚውን ሁለንተናዊ ግንኙነት (በትዳርም ይሁን በሌሎች ግንኙነቶች፤በሥራ ቦታ) ሊጎዳ ይችላል።
መጥፎ የአፍ ጠረን ሊያመጡ ከሚችሉ መንስኤዎች ውስጥ የሚከተሉት ይገኛሉ።
የአፍ ንፅህናን ያለመጠበቅ
የድድ ህመም መኖር
ሽታ ሊያመጡ የሚችሉ ባክቴሪያዎች በአፍና የአንጀት ክፍሎች ውስጥ መራባት
እንደ ካንዲዲያስስ ያሉ የፈንገስ ህመሞች መከሰት
የሳይነስ እንፎክሽን መድኃኒቶች(በተለይ አፍን የሚያደርቁ መድሃኒቶች)
ሲጋራ ማጨስ የተወሱ የምግብ ዓይነቶች(ነጭ ሽንኩርት፤ ሽንኩርት፤ ሰርዲን፤ ከፍተኛ የገንቢ ምግብ (ፕሮትን) ያላቸው ምግቦች)
የምግብ ያለመፈጨት ችግርና የጉበት ችግር የሆድ ድርቀት
መጥፎ የአፍ ጠረን መኖሩን እንዴት ሊያውቁ ይችላሉ?
መጥፎ ወይም የሚመር የአፍ ጣዕም ሲሰማዎት
በጣም የሚመከረው ዘዴ ግን የሚያምኑት ሰው መጥፎ የአፍ ጠረን እንደአለዎትና እንደሌለዎት እውነቱን እንዲነግሮት መጠየቅ ናቸው።
መጥፎ የአፍ ጠረንን ለመከላከል የሚመከሩ ነገሮች/ ምክሮች ምግብ ከተመገቡ በኋላ ጥርስዎትን መታጠብ (መቦረሽ)
ቢያንስ በቀን አንዴ በጥርስ መካከል ያሉትን የምግብ ተርፍራፊ በጥርስ መጎርጎርያ ወይም ፍሎስ ማዉጣት
ምላስዎትን መቦረሽ
አርትፊሽል ጥርስ ወይም ድድ ካለዎት ማፅዳት
የአፍ ድርቀትን መከላከል፣ ሲጋራ የሚያጨሱ ከሆነ ማቆም፤ውሃ በብዛት መጠጣት(ቡና፣ለስላሳ መጠጦችና አልኮል የአፍን መድረቅ ሊያመጡ ይችላሉ። ስለዚህ አያዘወትሩ)፤ማስቲካ ማኘክ ወይም ከረሜላ መምጠጥ።
ምንጭ፡- 8896 ሄሎ ዶክተር ኢትዮጵያ
የፌስቡክ ገጽ
አዲስ ዘመን ቅዳሜ ግንቦት 17/2011