ጅንጅቫይተስ (የድድ ኢንፍላሜሽን) ብዙ ጊዜ የሚከሰት የድድ ወይም የጥርስ ዙሪያ ላይ ህመም ሲሆን መቆጥቆጥ፣ ቅላትና እብጠት በድድዎ ላይ እንዲከሰት ያደርጋል::
ብዙውን ጊዜ ህመሙ መጠነኛ የሆነ ምልክት ስለሆነ ያለው ታማሚው ሳያስተውለው ሊያልፍ ይችላል::
ጅንጅቫይተስ በብዛት የሚከሰተው የአፍ ውስጥ ንፅህናን በደንብ በማይጠብቁ ሰዎች ላይ ሲሆን በዚህ የተነሳ በድድና ጥርስ ላይ የሚጋገር ነገር እንዲፈጠር ያደርጋል። ይህ የተጋገረው ነገር በግይን የማይታዩ ባክቴሪያዎችን የያዘ ነው። ጤናማ ድድ ጠንካራና ቀላ ያለ ሮዝ ቀለም ያለው ሲሆን የድድ ላይ ህመም ሲከሰት የሚከተሉትን ምልክቶች ሊያሳይ ይችላል።
• ጥርሶን በሚቦርሹበት (በሚፍቁበት) ወቅት በቀላሉ መድማት
• የላላ እና የተነፋ ድድ
• ሲነካ ህመም መኖር
• የድድ እብጠት
• የድድዎ መልክ መቀየር
• መጥፎ የአፍ ጠረን መከሰት ናቸው;;
ህመሙ እንዲባባስ የሚያደርጉት ደግሞ የሚ ከተሉት ናቸው።
• የአፍ ጤንነት (ንፅህና) በደንብ አለመጠበቅ
• ሲጋራ ማጨስ
• የስኳር ህመም
• እርጅና
• የአፍ ድርቀት
• የሆርሞን ለውጥ በተለይ በሴቶች ላይ እርግዝና ወቅት በወር አበባና የእርግዝና መከላከያ እንክብል በሚወስዱበት ጊዜ ሊከሰት ይችላል።
ታዲያ ይህን ህመም ለማከም በቤት ውስጥ ማድረግ የሚገቡን የህክምና ዘዴዎች አሉ።
- የጥርስ ህክምና ባለሙያው በሚያዘው መሰረት መደበኛ የሆነ የጥርስ እጥበት ማድረግ
- ለስለስ ያለ የጥርስ ቡርሽ መጠቀምና ቢያንስ በአንድ ወር ቢበዛ በሁለት ወራት መቀየር
- በቀን ሁለቴ አሊያም ከእያንዳንዱ ምግብ መርሕግብር በኋላ አፍዎን ማፅዳት
- የጥርስ ህክምና ባለሙያዎ ካዘዘልዎ የጥርስ ማጠቢያ አንቲሴፕቲክ መጠቀም ናቸው።
በሽታው የጥርስ ዙሪያ ላይ ህመም ቢሆንም በወቅቱ ካልታከመ ግን ወደ ከፋ ቀጣይ የህመም ደረጃ ይሸጋገራል። ይህ በሽታ ፔርዮዶንታቲስ የሚባል ሲሆን የጥርስ ደጋፊ የሆኑት የጥርስ አቃፊ አጥንትን የሚያጠቃ በሽታ ነው።በሽታው ድድን እና የጥርስ አቃፊ አጥንትን በመብላት፤ የሻህላ ክምችት በጥርሳችን እንዲኖር በማድረግ • መጥፎ የአፍ ጠረን
• የድድ በቀላሉ መድማት
• ማድዳችን እንዲሸሽ
• የጥርስ መነቃነቅ ብሎም
• የጥርስ መውለቅን ያስከትላል።
ምንጭ- ጤና ኢትዮጵያ ፌስቡክ ገጽ
አዲስ ዘመን ግንቦት 10/2011