ዩጋንዳ ጽንፈኝነትንና ስርዓት አልበኝነትን የሚቀሰቅሱ መልዕክቶችን አስተላልፈዋል ያለቻቸውን በ13 የሬዲዮና የቴሌቪዥን ጣቢያዎች የሚሰሩ ጋዜጠኞች ከስራ እንዲታገዱ ትዕዛዝ ሰጥታለች፡፡
የቢቢሲ ዘገባ እንደሚያመለክተው ትዕዛዙ የተሰጠው ለ13 የሬዲዮና ቴሌቪዥን ጣቢያዎች ሲሆን የኡጋንዳ ኮሚዩኒኬሽንስ ኮሚሽን የተሰኘው ተቆጣጣሪ ተቋም ለጣቢያዎቹ የተወሰኑ ጋዜጠኞቻቸውን እንዲያግዱ አዟል፡፡ ለራዲዮና ቴሌቪዥን ጣቢያዎቹ ከጋዜጠኞች በተጨማሪም የዜናና ፕሮግራም ኃላፊዎችንም እንዲያግዱ ትዕዛዝ ተላልፏል።
ኮሚሽኑ ጋዜጠኞቹን መረጃን አዛብቶ በማሰራጨት እንዲሁም ጽንፈኝነትንና ስርዓት አልበኝነትን የሚቀሰቅሱ መልዕክቶችን በማስተላለፍ ግጭት እንዲቀሰቀስ የሚያደርግ ስራ ሰርተዋል በሚል ወንጅሏቸዋል።
ተቋሙ ኤን ቢ ኤስ ቴሌቪዥን፣ ቡኬዴ ቴቪ፣ ኤንቲቪ፣ ሲቢኤስ ኤፍ ኤም፣ እና ካፒታልፍ ኤምን ጨምሮ ለ13 የሬዲዮና የቴሌቪዥን ጣቢያዎች የእርምጃ መልዕክት ልኳል። ለጣቢያዎቹ በደረሳቸው መልዕክት በዝርዝር ምን ዓይነት ጥፋት እንደፈጸሙ የሚያሳይ ጉዳይ (ኬዝ) አልተጠቀሰላቸውም ተብሏል።
በሶስት ቀናት ውስጥ አዘጋጆችን፣ የዜና እና የፕሮግራም ኃላፊዎችን እንዲያግዱ ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣቸው ነው የተነ ገረው። ጣቢያዎቹ በቀጥታ ስርጭት፣ በሰበር ዜና፣ በመፅሄት ፕሮግራሞችና በዋና የዜና ሰዓታት የብሮድካስቲንግ ዝቅተኛ መስፈርትን የሚጥሱ ይዘቶች በማሰራጨታቸው እር ምጃው እንደተወሰደባቸው ኮሚሽኑ ገልጿል።
አዲስ ዘመን ሚያዝያ 25/2011
በየትናየት ፈሩ