ዘመን አይሽሬው የሥነ-ጽሁፍ ፈርጥ በቲያትር

በተባ ብዕሩ ዘመን አይሽሬ የስነ ጽሁፍ ሥራዎችን ለተደራሲን አቅርቧል፡፡ በቀደምት መጽሔቶችና ጋዜጦች ልዩ ልዩ ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ወቅታዊ ጉዳዮችን የሚዳስሱ ጽሁፎችን ለአንባቢያን ጀባ ብሏል፡፡ በውጭ አገራት ተምረው ከመጡ ሌሎች ኢትዮጵያውያን ጋር በመሆን... Read more »

የጉማ ሽልማት ለፊልም መነቃቃት

በየዓመቱ የሚካሄደው ጉማ የፊልም ሽልማት ከተጀመረ እነሆ ዘንድሮ 9ኛ ዙር ላይ ደርሷል፡፡ ባለፈው አርብ ሰኔ 2 ቀን 2015 ዓ.ም የ9ኛው ዙር የጉማ ፊልም አሸናፊዎች ታውቀዋል፡፡ ጉማ የፊልም ሽልማት የፊልም መነቃቃት ይፈጥራል፤ ፈጥሯልም፡፡... Read more »

አወዛጋቢው የመጻፊያ ቋንቋና ሥነጽሑፋችን

የኢትዮጵያ ሥነጽሑፍ የደለበ ታሪክ ባለቤት ነው። ይህንንም በርካቶች፣ ከውስጥም ከውጭም ተደጋጋሚ ጊዜያት ለአደባባይ ያበቁት ጉዳይ ነው። የኢትዮጵያ ሥነጽሑፍ የቱንም ያህል የደለበ ታሪክ ይኑረው እንጂ እንደ ትልቅ ታሪክ ባለቤትነቱ የዓለም የሥነጽሑፍ አደባባይ ላይ... Read more »

ካርማ

የ«ካርማ» ቀጥተኛ ፍቺ፣ ከቶ የማይዛነፍ፣ የድርጊትና የውጤት ግንኙነት ነው። ድርጊቱ ሰላማዊ ከሆነ ውጤቱም ሰላማዊ፤ ድርጊቱ ጦርነት ከሆነ ውጤቱም ያንኑ ጦርነትና እልቂት ይሆናል ማለት ነው። የእኛን ባህላዊ አገላለፅ መሠረት አድርገን ስንመለከተው ደግሞ «የእጅህን... Read more »

የሂሩት በቀለ- ወርቃማ ዘመናት

መስከረም 28 ቀን 1935 ዓ.ም አዲስ አበባ ‹‹ቀበና›› ከተባለ አካባቢ የተወለደችው ህጻን ልጅነቷን ባሳለፈችበት ዕድሜ የተለየ ተሰጥኦ እንዳላት የነገራት አልነበረም። እሷም ብትሆን ውስጧ የቆየውን ድብቅ ችሎታ በወጉ ሳታውቀው አመታትን አብራው ዘልቃለች። ሂሩት... Read more »

አርበኝነት በጥበብ ሥራዎች

ባለፈው አርብ ሚያዝያ 27 ቀን 2015 ዓ.ም 82ኛው የአርበኞች ቀን በአራት ኪሎ የድል አደባባይ ተከብሯል:: ከዚህ በተጨማሪም በተለያዩ መገናኛ ብዙኃን ክስተቱን የሚያስታውሱ የታሪክና የኪነ ጥበብ ሥራዎች ቀርበዋል:: በማግስቱ በነበሩት የቅዳሜና እሁድ የመገናኛ... Read more »

የጥላሁን ገሰሰ – ሰበበኛ ዜማዎች

 1933 ዓ.ም ዕለተ መስቀል። ለአቶ ገሰሰ ቤተሰብ አውደዓመት ሆኖ ብቻ አላለፈም። ከቀኑ መከበር ጋር ለጎጇቸው ሌላ የምሥራችን ይዞ ደረሰ። እማወራዋ ጌጤ ጉሩሙ ወንድ ልጅ ከነቃጭሉ መገላገላቸው በቤቱ ታላቅ ደስታን ፈጥሮ ዋለ። በዓሉ... Read more »

ተተኪ ድምፃውያንን በ «ባላገሩ ምርጥ»

የሰዎችን ቀልብ ከሚገዙና አዝናኝ የኪነ ጥበብ ዘውጎች ውስጥ አንዱ ሙዚቃ ነው። ሙዚቃ ከአዝናኝነቱ ባሻገር በርካታ ማህራበዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊና ሌሎችም ሀገርኛ መልዕክቶች የሚተላለፉበት የጥበብ ዘርፍ ነው። በሙዚቃ ፍቅር፣ አንድነት ፣ መተሳሰብና አብሮነት ይሰበካል።... Read more »

 ረመዳንን በመንዙማ

የኢትዮጵያ ታሪክና መንዙማ የሚጀምረው ቁርአን መቀራት ከያዘበት ዘመን አንስቶ መሆኑ ይነገራል። ነብዩ መሐመድና የኢትዮጵያውያን ታሪክ መሠረት በውል የተጋመደ ነው። ቢላልን ጨምሮ፣‹‹ሱሀባዎች›› የተሰኙ የነብዩ ረዳቶች፣ ሞግዚታቸው እሙ አይመንና የሌሎች በርካቶች ማንነት ከኢትዮጵያ የዘር... Read more »

 ዘለሰኛና ሰሞነ ሕማማት

እየሱስ ክርስቶስ የአዳምን በደል ለመሻር ከሰማየ፣ ሰማያት ወርዶ ከድንግል ማርያም ተወልዶ ሰላሳሦስት ዓመታትን በምድር ሲያስተምር ኖረ። ጊዜው ሲደርስ በራሱ ፈቃድና በአይሁድ ክፋት ከፍ ያለ መከራን ሊቀበል፣ ከመስቀል ተቸንክሮ ሊሰቀል ግድ ሆነ። ሞት... Read more »