መንግሥትንስ ማን ይቆጣጠረው?

ያለአግባብ የተጋነነ ዋጋ የሚጨምሩና ምርት የሚደብቁ ስግብግብ ነጋዴዎችን በተመለከተ ብዙ ተብሏል። መንግሥት ተገቢውን ቁጥጥር እንዲያደርግ ብዙ አስተያየቶች ተሰጥተዋል። የምርም ደግሞ መንግሥት ቁጥጥር እያደረገ ነው። ብዙ ነጋዴዎች ላይ ርምጃ ተወስዷል፤ እንደ ጥፋታቸው መጠን... Read more »

የክረምቱ ነገር …

መቼም የክረምት መልኮች ብዙ ናቸው። ቆም ብለን ሁኔታዎችን እንታዘብ ካልን ደግሞ አጋጣሚዎች በየአቅጣጫው ያሣዩናል። ክረምቱ ሲቃረብ፣ ዝናቡ ‹‹መጣሁ›› ሲል ዓእምሯችን አስቀድሞ የሚያስበው አይጠፋም። ክረምት በባህርይው እንደበጋው ደረቅ አይደለምና ቀድመው ቢፈሩት፣ ቢጠነቀቁት አይገርምም።... Read more »

የትርክት ዕዳ እና ድህነት

ዲያቆን ዳንኤል ክብረት የጻፈው ‹‹የትርክት ዕዳና በረከት›› መጽሐፍ ባለፉት ሳምንታት አጀንዳ ሆኖ ቆይቷል:: በፋና እና በዋልታ ቴሌቪዥን ቀርቦ ለጥያቄዎች መልስና ማብራሪያ ሰጥቷል:: ከመጽሐፉም ሆነ ከጸሐፊው ተጨማሪ ማብራሪያዎች (በቃለ መጠይቆች) የምንረዳው ነገር የትርክት... Read more »

ከፀሐይ እና ከጨረቃ እምነትንና እውነትን ፍለጋውድ

የሰው ልጅ በእምነትና በእውነት ላይ በመንገሥ (በመቆም) ህልውናውን የሚገነባ እና የሚተክል የማንነቱ ባለዳ ነው። አንድም ሰሪ፣ አንድም ተሰሪ ነው። የእምነቱም ፤ የእውነቱም ማረጋገጫ ወይም መግለጫ ሀሰሳው ሩቅና ጠናና ነው። ከሙከራዎቹ መካከል ጨረቃንና... Read more »

‹‹አትቀጡብኝ›› ልመና!

ባለፈው እሮብ ነው። አራት ኪሎ ባሻ ወልዴ ኮንዶሚኒያም አካባቢ ከአንድ ምግብ ቤት ምሳ ልበላ ተቀምጫለሁ። የአዲስ አበባ ፖሊስ መለያ ያለው አንድ ተሽከርካሪ የድምፅ ማጉያ (ማይክራፎን) ተገጥሞለት ልመና መሰል ማስጠንቀቂያ እየሰጠ ወዳለሁበት ቦታ... Read more »

መካከለኛው መደብ ጭቁን ወይስ ሥልጡን?

አንዳንድ ሰዎች የአንድን ሰው አለመሰልጠን ለመግለጽ ‹‹ዝግመተ ለውጡን ያልጨረሰ›› እያሉ ሲሳደቡ እንሰማለን። ስድቡ ነውር መሆኑ እንዳለ ሆኖ ልብ ያልተባለው ነገር ግን የተጠየቅ ስህተት ያለበት መሆኑ ነው። ዝግመተ ለውጥ አያልቅም። የአሁኑ ሆሞ ሳፒያንስ... Read more »

እነ ሰበቡ…

አበው ሲተርቱ ‹‹ክፉ ቀን አይምጣ›› ይላሉ፡፡ይህን ያሉት ደግሞ ያለምክንያት አይደለም፡፡በክፉ ቀናት ክፉ የሚባሉ ሰዎች ቢገጥሟቸው እንጂ፡፡ አንዳንዴ በገጠመኝ የሚከሰቱ እውነታዎች ይህን ተረት ደጋግመን እንድናስታውሰው ያስገድዱናል፡፡ አጋጣሚዎቹ እንደ ቃሉ ይዘት ክፉ የሚባል ደረጃ... Read more »

ቦንዳ ከፍርሃት ወደ ኩራት

ቦንዳ የሚለውን ቃል ለመጀመሪያ ጊዜ የማውቀው ልጅ እያለሁ በአካባቢያችን ልብስ የሚሰፉ ሰዎች የሚሸጡት ብትን ጨርቅ ነበር:: ልብስ የሚያሰፉ ሰዎች ተለክተው ከብትን ጨርቁ የመረጡትን አይነትና ቀለም አዝዘው ይሄዳሉ:: ይሄው ብትን ጨርቅ የጣውላ ቅርጽ... Read more »

‹‹ዋው! ሀገራችን!›› ‹‹ኤጭ! ይቺ ሀገር!››

አንዳንድ የማይቻል የሚመስሉ ምኞቶቼ ተሳክተዋል:: የማይቻል ይመስሉኝ የነበረው የማይቻሉ ሆነው ሳይሆን ባለን ኋላቀር አመለካከት ምክንያት ነበር:: ልጅ ሆነን ከአካባቢያችን በጣም የራቀ አካባቢ (የሰማይ አድማስ የሚታይበት) ቦታ እየጠቆምን ‹‹ክንፍ ቢኖረኝና ብርርርር ብየ እዚያ... Read more »

የቅድመ ቁጣ አገልግሎት ሰጪዎች

በብዙ አገልግሎት መስጫ ተቋማት ውስጥ አገልግሎቱን የሚሰጡ ሠራተኞች ሲቆጡና ሲያመናጭቁ ማየት የተለመደ ነው:: ምንም እንኳን ግልምጫና ስድብ ትክክል ባይሆንም፤ ቢያንስ ግን ተገልጋዩ ያለአግባብ ልስተናገድ ብሎ ካስቸገረ በኋላ አይሻልም? እንዴት የዱቤ ይቆጣሉ? መጀመሪያ... Read more »