ፕሬዝደንት ሣሕለወረቅ ዘውዴ ወደ ቪየና ኦስትሪያ ተጓዙ

የኢፌዴሪ ፕሬዝደንት ሣሕለወረቅ ዘውዴ በአፍረካና አውሮፓ ህብረት ፎረም ላይ ለመሳተፍ ወደ ቪየና ኦስትሪያ ተጓዙ። በነገው እለት የሚካሄደው ፎረም በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጅ ልማት ላይ ትኩረት ሰጥቶ ይነጋገራል። ፕሬዚዳንት ሣሕለወረቅ ዘውዴ በቆይታቸው በፎረሙ ላይ ኢትዮጵያ... Read more »

”ህዝብ እንደ ህዝብ ሊጣላ አይችልም ከፍቅር ውጪ የሚያውቀው አጀንዳ የለውም”- ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል 

“ህዝብ እንደ ህዝብ ሊጣላ አይችልም ከፍቅር ውጪ የሚያውቀው አጀንዳ የለውም” ሲሉ የኢህዴግ ሴቶች ሊግ ሊቀመንበር እና የሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል ገለፁ። 4ኛው የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) ሴቶች ሊግ ጉባኤ... Read more »

በኢትዮጵያ የማንበብ ባህል እንዳልዳበረ ተገለጸ

በኢትዮጵያ የማንበብ ባህል እንዳልዳበረና በቀን አንድ ገፅ ካለንባብ የሚያሳልፈው ዜጋ በርካታ መሆኑን የብሄራዊ ቤተመፃህፍትና ቤተመዛግብት ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡ በኢትዮጵያ የንባብ ባህልን ለማሳደግ በክልሎች ቤተመዛግብትና ቤተመፃህፍቶችን ለማደራጀት እየተሰራ መሆኑም ተጠቁሟል፡፡ በህንድ አንድ ሰው በሳምንት... Read more »

አቶ አወል አርባ ኡንዴ የአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ሆነው ተሾሙ።

የክልሉ ምክር ቤቱ 5ኛ ዙር 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 2ኛ አስቸኳይ ጉባኤውን እያካሄደ ይገኛል። በዚህም አቶ አወል አርባን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አድርጎ ሾሟል። አቶ አወል አርባ የአፋር ብሄራዊ ዴሞክራሲዊ ፓርቲ (አብዴፓ) ምክትል... Read more »

የሀዋሳ የኤሌክትሮኒክስ ግብይት ማዕከል ተመረቀ

የኢትዮጵያ ምርት ገበያ በ12 ሚሊየን ብር ያስገናባውን የሀዋሳ የኤሌክትሮኒክስ ግብይት ማዕከል አስመረቀ። የኢትዮጵያ የምርት ገበያ ለፋና ብሮድ ካስቲንግ በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው የሀዋሳ የኤሌክትሮኒክ ግብይት ማዕከል ግንባታ ተናቅቆ ታህሳስ 6፣ 2011 ለአገልግሎት ክፍት... Read more »

የአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የክልሉ ምክር ቤት የአስፈጻሚ አካላትን እንደገና ለማደራጀት የቀረበውን አዋጅም በሙሉ ድምጽ አጽድቋል፡፡

ምክር ቤቱ የሚከተሉት ቢሮዎች በአዋጅ ተቋቁመዋል 1 የሰላምና ጸጥታ ቢሮ  2 የጠቅላይ አቃቢ ህግ መስሪያ ቤት 3 የገቢዎች ቢሮ 4 የቴክኒክ ፣ ሙያ እና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ 5 የመንገድ ልማት እና ትራንስፖርት... Read more »

አባገዳዎች፣ የአገር ሽማግለዎችና የሃይማኖት አባቶች ከሶማሊላንድ የሃይማኖት አባቶች ጋር ተወያዩ

የቀድሞ አባገዳ በየነ ሰንበቶ በልዑካን ቡድኑ ውስጥ ተሳትፈዋል፡፡ በኢትዮጵያ የሶማሊላንድ አምባሳደር አህመድ ኤልጋ በውይይቱ ላይ እንደገለጹት፣ ውይይቱ የህዝብ ለህዝብ ውይይት ላይ ያተኮረ ነው፡፡ አበገዳዎች፣ የሃይማኖት አባቶችና የአገር ሽማግሌዎች በሶማሊላንድ ቆይታቸው የበርበራ ወደብን... Read more »

የቀድሞ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ የአይን ብሌናቸውን ለመለገስ ቃል የገቡ የመጀመሪያ ኢትዮጵያዊ ሆኑ

የቀድሞ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ግርማ ወ/ጊዮርጊስን የአይን ብሌናቸውን ለመለገስ ቃል የገቡ የመጀመሪያ ሰው መሆናቸውን የኢትዮጵያ የአይን ባንክ ገለጸ፡፡ የቀድሞ ፕሬዝዳንት በ12 አመት የፕሬዝዳንትነት ቆይታቸው የተለያዩ ሰብዓዊ ድጋፍ የሚሰጡ ተቋማትን በማቋቋም ይታወሳሉ፡፡ ግርማ ወ/ጊዮርጊስ... Read more »

ክለቦቹ ለሰብአዊነት ቅድሚያ ሰጥተው እየሰሩ ነው

‹‹ከእግር ኳስ ደጋፊዎች 50 ሺህ 315 ብር ተሰብስቧል፤ የተሰበሰበው ገንዘብ በማረሚያ ቤት ከፍተኛ የአካል እና የስነ-ልቦና ጉዳት ለደረሰበት ለአቶ ዮሀንስ ጋሻው እና ለተፈናቃዮች የሚውል ነው፡፡›› የባሕርዳር ከነማ እና ኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ... Read more »

‹‹ከ9 ሺህ ቶን በላይ የማር ምርት ተገኝቷል፡፡›› የአማራ ክልል እንስሳት ሀብት ልማት ማስፋፊያ ኤጀንሲ

በአማራ ክልል ከ9 ሺህ ቶን በላይ የማር ምርት መገኘቱን የአማራ ክልል እንስሳት ሀብት ልማት ማስፋፊያ ኤጀንሲ አስታወቀ። የአማራ ክልል ለንብ ማነብ ተስማሚ የሆነ የአየር ፀባይ እና የመልክዓ ምድር አቀማመጥ እንዳለው ይነገራል፡፡ በአሁኑ... Read more »