አብሮ አደግነት ያመሳቀለው ሕይወት

ልጅነት አታላይ ነው። በትምህርት የታገዘ ግንዛቤ ካልታከለበት የወደፊቱን ያበላሻል። በጓደኛ ግፊት ብቻ አይወድቁ አወዳደቅ ላይ ይጥላል። የወደፊቱን ዕጣ ፈንታ ብልሽትሽቱን ያወጣዋልም። የተበላሸውን ለማስተካከል ደግሞ ብዙ ዋጋ ያስከፍላል። በተለይ ብዙ ወጣት ሴቶች እንዲህ... Read more »

ከጅብ ጋር እየተጋፉ፣ ቅጠል ለቅመው በመሸጥ ቤተሰባቸውን የሚያስተዳድሩት መነኩሴ

እማሆይ ሙሉዓለም ፈረደ ይባላሉ። አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ፈረንሳይ ኬላ አካባቢ ነዋሪ ናቸው። እንጨት ለቅሞ፣ ቅጠል ጠርጎ በመሸጥ እራሳቸውን እና አምስት ቤተሰብ የማስተዳደር ኃላፊነት ወድቆባቸዋል። በዚህ ስራ ወደ እንጦጦ ሲያቀኑ፣ በአጋጣሚ ከጅብ... Read more »

በበደል የተገፋውና በጥረቱ መሰንበት የቻለው ጫማ ሰፊ

የትምህርት ዕድል አለማግኘት፣ ምግብና መጠለያ ማጣት ከተስፋ መቁረጥ ጋር ሲደመር ድህነትን ይወልዳል። እነዚህን የሕይወት ውጣውረዶችን አልፎ በሕይወት ለመኖር የሚታትር፣ ልመናን የተጠየፈ ዜጋ ማግኘት ብዙም ያልተለመደ ነው። የዛሬው የዚህ ዓምድ እንግዳችን እናቱ፣ እህትና... Read more »

በ”ኮስትር‘ የተለኮሰው ገጣሚ

በሹፌርነት የሥራ መስክ ተሰማርተው ነው የሚገኙት። በሙያው ለመሰማራት የበቁት የ12ኛ ክፍል ፈተና (ማትሪክ) ውጤታቸው ዩኒቨርሲቲ ሊያስገባቸው ስላልቻለ ነው። ይህ ባይሆን ኖሮ ምናልባትም ዛሬ በሥነ ጽሑፉ ዓለም አንቱ በተባሉ፤ ስንትና ስንትም የድርሰት ሥራዎቻቸውን... Read more »

ሰዓሊው ያልተሻገረው የሕይወት ምስቅልቅል

እጅ እግር ያለው ሊቋቋመው የማይችለው ፈተና በአካል ጉዳተኛ ላይ ሲደርስ በሕይወት ዘመን የሚፈጥረው ጫና እጅግ ከባድና ለማመን የሚቸግር ነው። ያውም በተፈጥሮ እጅ እግሩ የማይሠራ ሆኖ ለተወለደ ሰው የሚያሳድረው ስነልቦናዊ ጉዳት በቃላት አይገለፅም።... Read more »

የበቆሎ ሻጯ ራስን ችሎ የመኖር ፈተና

ከምሽቱ አስራ ሁለት ሰዓት አካባቢ ነው፡፡ እኔና ባልደረባዬ ከሥራ እንደወጣን የእግር እንቅስቃሴ እያደረግን ወደ ቤታችን ለመሄድ በማሰብ ከአራት ኪሎ ፒያሳ፤ ከፒያሳ የቸርችል ጎዳናን ይዘን ቁልቁል ወደ ለገሀር እያዘገምን ነው፡፡ ቸርቸል ጎዳና አዲስ... Read more »

ዛፍ ቆረጣን መተዳደሪያ ያደረጉት ጎልማሳ

በአረንጓዴ አሻራ ንቅናቄ ላይ እያለን ስለዛፍ ቆራጭ ማውራት ምቾት ላይሰጠን ይችላል:: ያውም ችግኞችን መትከል፣ ዛፎችን መንከባከብ የህይወታችን መርህ አድርገን በተነሳንበት በዚህ ወቅት:: ‹‹ዛፍ ቆራጩ›› ያልናቸው እኚህ ሰው ግን በየመንደሩ አደጋ ያደርሳሉ የተባሉ... Read more »

በእንብርክኩ ተጉዞ የተማረው አካል ጉዳተኛ የህይወት ውጣ ውረድ

ራሲሞ ከባ ይባላል። የተወለደው በምዕራብ ወለጋ ዞን መንዲ ወረዳ ነው። ለቤተሰቡ አራተኛና የመጨረሻ ልጅ ሲሆን ሦስት ታላላቅ እህቶች አሉት። አባቱ ገና የዘጠኝ ወር ልጅ እያለ ነው የሞቱት። እንደአባትም እንደእናትም ሆነው ያሳደጉት እናቱ... Read more »

ጫማ ጠርጋ አደሯ የልጆች እናት

አንዳንድ ጊዜ አዕምሯችን የተማርነውንና ዓለምን የተረዳንበትን መንገድ አስቶን ያደግንበትን ማህበረሰብ ኋላ ቀር አስተሳሰብ፤ ጎጂ ባህልና ወግ አድንወርስ ያደርገናል። እንደህሊናችን ሳይሆን እንደ አካባቢያችንና እንደ ማህበረሰባችን እንድናድር፤ ምክንያታዊነትን ትተን ዘልማዳዊ እንድንሆን ይጫነናል። ለምሳሌ፡- የቤት... Read more »

መኪና በማጠብ ኑሮውን የሚገፋው የቀድሞው የኢትየጵያ ወታደር

ህይወት ባሰቧት መንገድ የማትሄድ መልከ ብዙ ነች። ጥቂቶች ህልማቸውን እውን ያደርጋሉ። ባሰቡት የህይወት መስመር ትልቅ ደረጃ ላይ ለመድረስ አስበው በተለያዩ ምክንያቶች ከጉዟቸው ተደነቃቅፈው መንገድ ላይ የሚቀሩ በርካቶች ናቸው። በአንድ ወቅት ዳጎስ ያለ... Read more »